እስልምና እና ሽብርተኝነት
ማርክ ኤ. ገብርኤል
ቅንብር በአዘጋጁ

 

ክፍል አንድ 

የእኔ ታሪክ

 

 

 

በአል-አዝሃር ግራ መጋባት

 

ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት ታዋቂዎቹ የግብፅ ፒራሚዶች በሚገኙባት ጊዛ በተባለች የግብፅ ከተማ ውስጥ የሚገኝ መስጊድ ኢማም ነበርኩኝ፡፡ (የመስጊድ ኢማም ስልጣን አንድ መጋቢ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ካለው ደረጃ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡) አርብ ከቀኑ ስድስት ሰዓት እስከ ሰባት ሰዓት ድረስ የሳምንቱን የስብከት መልዕክት ማስተላለፍ እና ሌሎች ኃላፊነቶችን እወጣ ነበር፡፡

 

አንድ አርብ ቀን የመለዕክቴ ርዕስ ጂሃድ የሚል ነበር፡፡ በፊቴ የተቀመጡትን ሁለት መቶ ስድሳ የሚያክሉ ሰዎችን እንዲህ በማለት ነገርኳቸው፡

 

በእስልምና ጂሃድ ማለት የእስልምናን ሃገር እና እስልምናን ከጠላት ጥቃቶች መከላከል ነው፡፡ እስልምና የሰላም ኃይማኖት ስለሆነ የሚዋጋው የሚዋጉትን ብቻ ነው፡፡ እነዚህ ከሃዲያን፣ አረማውያን፣ ጠማሞች፣ ክርስቲያኖች እና አላህን አሳዛኝ የሆኑት አይሁዶች ሰላማዊ በሆነው በእስልምና እና በነቢዩ ከመቅናታቸው የተነሳ እስልምና በሰይፍ እና በሽብር እንደተስፋፋ ይናገራሉ፡፡ እነዚህ ከሃዲያን፣ የእስልምና ከሳሾች የሆኑት ሰዎች ለአላህ ቃል ዕውቅናን ይነፍጋሉ፡፡

 

ቀጠል በማድረግም የሚከተለውን የቁርአን ቃል ጠቀስኩኝ፡

 

ያቺንም አላህ ያወገዛትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ፡፡ የተበደለም ኾኖ የተገደለ ሰው ለዘመዱ (በገዳዩ ላይ) በእርግጥ ስልጣንን አድርገናል፡፡ (ሱራ 17፡33)

 

እነዚህን ቃላት በተናገርኩበት ጊዜ በዓለም ላይ ከሁሉም የተሻለ ተቀባይነት ካለው እድሜ ጠገብ ከሆነው በግብፅ የካይሮ ከተማ ከሚገኘው የአል-አዝሃር ዩኒቨርሲቲ ገና ተመርቄ መውጣቴ ነበር፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለእስልምና እንደ መንፈሳዊ ባለ ሥልጣን ያገለግላል፡፡ በዩኒቨርሲቲው ውስጥም እያስተማርኩኝ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ደግሞ በዚህ መስጊድ ውስጥ እንደ ኢማም አገለግል ነበር፡፡

 

በዚያን ዕለት ስለ ጂሃድ የሰበክሁት በግብፅ መንግሥት ፍልስፍና መሰረት ነበር፡፡ የአል-አዝሃር ዩኒቨርሲቲ ፖለቲካዊ ትክክለኝነት ባለው እስልምና ላይ በማተኮር ከግብፅ መንግሥት አመለካከት ጋር የሚጋጩ ትምህርቶችን ሆነ በማለት ገሸሽ ያደርግ ነበር፡፡

 

እነርሱ ያስተማሩኝን እያስተማርኩ ያለሁ ቢሆንም ነገር ግን በውስጤ ስለ እስልምና እውነት ግራ ተጋብቼ ነበር፡፡ በአል-አዝሃር ያለኝን ሥራ እና ደረጃ ማስጠበቅ ካለብኝ ግን አመለካከቴን ለራሴ ብቻ መያዝ ግድ ይለኛል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ከአል-አዝሃር አጀንዳ የተለየ አቋም የነበራቸው ሰዎች የደረሰባቸውን ጠንቅቄ አውቅ ነበር፡፡ በቀጥታ የሚባረሩ ሲሆን በሃገሪቱ ውስጥ በሚገኝ በማንኛውም ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ማስተማር እንዳይችሉ እግድ ይጣልባቸው ነበር፡፡

 

በመስጊድ እና በአል-አዝሃር ውስጥ የማስተምረው ነገር ገና የአስራ ሁለት ዓመት ልጅ ሳለሁ ሙሉ በሙሉ በሸመደድኩት ቁርአን ውስጥ የማየው እንዳልሆነ ይገባኝ ነበር፡፡ ከሁሉም በላይ ግራ ያጋባኝ ደግሞ የፍቅር፣ የቸርነት እና የይቅርታ እስልምናን እንድሰብክ የተነገረኝ መሆኑ ነው፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ እውነተኛውን እስልምና እንዲተገብሩ የሚጠበቁት አክራሪ ሙስሊሞች አብያተ ክርስቲያናትን በቦምብ ያጋዩ ነበር፤ ክርስቲያኖችንም ይገድሉ ነበር፡፡

 

በዚያን ጊዜ በግብፅ ውስጥ የጂሃድ እንቅስቃሴ ተጋግሎ ነበር፡፡ በክርስቲያኖች ላይ የሚፈፀሙ የቦምብ ጥቃት ዘገባዎችም የተለመዱ ነበሩ፡፡ ይህ ተግባርም የየዕለት ኑሮ አካል ከመሆኑ የተነሳ አንድ ጊዜ በአውቶብስ ስሄድ ሳለሁኝ ቦምብ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲፈነዳ ሰምቼ ነበር፡፡ አሻግሬም ስመለከትም በግማሽ ማይል ርቀት ቦታ ላይ ጢስ ወደላይ ሲጉተለተል ማየት ችዬ ነበር፡፡

 

በእስልምና በጣም በፀና ቤተ ሰብ ውስጥ ያደግሁኝ ሲሆን የእስልምናንም ታሪክ አጥንቼ ነበር፡፡ በየትኛውም የፅንፈኛ ሙስሊሞች እንቅስቃሴ ውስጥ አልተሳተፍኩም ነገር ግን ከጓደኞቼ መካከል አንዱ ክርስቲያኖችን በመጨፍጨፍ በሚታወቅ እስላማዊ ቡድን ውስጥ አባል ነበር፡፡ ምፀታዊው ነገር የኬሚስትሪ ተማሪ የነበረ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነበር እምነቱን አጥብቆ የያዘው፡፡ የሆነው ሆኖ ጂሃድ ውስጥ በንቃት ይሳተፍ ነበር፡፡ አንድ ቀን እንዲህ በማለት ጠየቅሁት፡ “አብሮ አደጎቻችን የሆኑትን ጎረቤቶቻችንን እና የሃገራችንን ሰዎች የምትገድለው ስለምንድነው?”

 

በጣም ተናደደ፤ ከጥያቄዬም የተነሳ በጣም ተገረመ፡፡ “ከሁሉም አስቀድሞ እናንተ ሙስሊሞች ይህንን ጉዳይ ማወቅ ነበረባችሁ፡፡ ክርስቲያኖች የእስልማናን ጥሪ አይቀበሉም፤ እምነታቸውን ደግሞ መለማመድ ይችሉ ዘንድ ጂዝያን ለመክፈል ፈቃደኞች አይደሉም፡፡ ስለዚህ ያላቸው ብቸኛው አማራጭ የእስልምና ሕግ ሰይፍ ብቻ ነው፡፡”

 

እውነትን መፈለግ

 

ከእርሱ ጋር ካደረግሁት ንግግር የተነሳ እርሱ የተናጋረውን የሚቃረን ነገር አገኛለሁ በሚል ተስፋ በቁርአን እና በእስላማዊ ሕጎች መጻሕፍት ላይ ትኩረቴን አደረግሁኝ፡፡ ያነበብኩትን እውነታ ግን መለወጥ አልተቻለኝም፡፡

 

እንደ ሙስሊም ያለኝ አማራጭ ሁለት ብቻ መሆኑን ተገነዘብኩኝ፡

 

  • “ክርስቲያናዊ” የሆነውን እስልምና መከተሌን መቀጠል እችላለሁኝ - የሰላም፣ የፍቅር፣ የይቅርታ እና የርህራሄ እስልምና - ከግብፅ መንግሥት፣ ፖለቲካ እና ባሕል ጋር አብሮ እንዲሄድ ተለክቶ የተሰፋውን እስልምና በመከተል ስራዬን እና ደረጃዬን መጠበቅ እችላለሁ፡፡

  • የእስላማዊ እንቅስቃሴ አባል በመሆን በቁርአን እና በመሐመድ አስተምሕሮ መሰረት እስልምናን መከተል እችላለሁኝ፡፡ መሐመድ እንዲህ ብሎ ነበር፡ “ከአንድ ነገር ጋር እተዋችኋለሁ [ቁርአን]፡፡ የተውኩላችሁን ነገር አጥብቃችሁ ከያዛችሁ ለዘለዓለም በተሳሳተ መንገድ አትሄዱም፡፡”

 

ብዙ ጊዜ ለራሴ እንዲህ በማለት እየተለማመድኩ ያለሁትን የእስልምና ዓይነት ምክንያታዊ ለማድረግ እሞክር ነበር፣ አንተ ያን ያህል ርቀህ የሄድክ አይደለህም፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ በቁርአን ውስጥ ስለ ፍቅር፣ ሰላም፣ ይቅርታ እና ምህረት የሚናገሩ ብዙ ጥቅሶች አሉ፡፡ ስለ ጂሃድ እና ሙስሊም ያልሆኑትን ሰዎች ስለመግደል የሚናገሩትን ጥቅሶች ብቻ ችላ ማለት ነው የሚኖርብህ፡፡

 

ጂሃድን እና ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችን መግደልን ለማስወገድ ወደ ሁሉም ዓይነት የቁርአን ፍታቴ ሄድኩኝ ነገር ግን ለድርጊቱ ድጋፍ የሚሰጡ ነገሮችን ማግኘቴን ቀጠልኩኝ፡፡ ሙስሊሞች በካሃዲዎች (እስልምናን በማይቀበሉት ሰዎች) ላይ እና እስልምናን በመተው ወደ ኋላ በሚመለሱት ሰዎች ላይ ጂሃድን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸው ምሑራን ይስማማሉ፡፡ ነገር ግን የጂሃድ ጥቅሶች ከሰዎች ጋር በሰላም ስለመኖር ከሚናገሩት ከሌሎች ጥቅሶች ጋር አብረው አይሄዱም፡፡

 

በቁርአን ውስጥ የሚገኙት ተቃርኖዎች በሙሉ ለእምነቴ ችግርን መፍጠር ጀመሩ፡፡ የመጀመርያ ዲግሪዬን ለማግኘት አራት ዓመታትን አጥፍቼአለሁኝ፤ ስድስት ሺህ ተማሪዎችን ከያዘ የትምህርት ክፍል ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቄአለሁኝ፡፡ ከዚያም የማስተርስ ዲግሪዬን ለመያዝ አራት ዓመታት እና የዶክትሬት ዲግሪዬን ለመያዝ ደግሞ ሦስት ዓመታት ነበሩ፡፡ ይህ ሁሉ እንግዲህ እስልምናን ለማጥናት ነበር፡፡ ትምህርቶችንም እንደዚሁ አውቃቸዋለሁ፡፡

 

አንድ ቦታ ላይ አልኮል ተከልክሏል ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ ተፈቅዷል (ሱራ 5፡90-91 ከሱራ 47፡15 ጋር ያነፃፅሩ)፡፡ በአንድ ቦታ ላይ ቁርአን ክርስቲያኖች እውነተኛውን አንዱን አምላክ የሚያመልኩ በጣም ጥሩ ሰዎች እንደሆኑ እና ከእነርሱም ጋር መወዳጀት እንደሚቻል ናገራል (ሱራ 2፡62፣ 3፡113-114)፡፡ ነገር ግን ደግሞ ክርስቲያኖች መለወጥ እንደሚኖርባቸው፣ ግብርን መክፈል እንዳለባቸው እና ይህ ካልሆነ ግን በሰይፍ መገደል እንዳለባቸው ይናገራል (ሱራ 9፡29)፡፡

 

ምሑራኑ ለነዚህ ሁሉ ሥነ-መለኮታዊ ምላሽ አላቸው ነገር ግን ሁሉን ሁሉን ቻይ እና ሃያል የሆነው አላህ ለምን እጅግ ራሱን እንደሚቃረን ወይንም ደግሞ ለምን እጅግ አቋሙን እንደሚቀያይር ይደንቀኝ ነበር፡፡

 

የእስልምና ነቢይ የሆነው መሐመድ እንኳ እምነቱን ይለማመድ የነበረው ቁርአንን በሚቃረን መንገድ ነበር፡፡ ቁርአን እንደሚናገረው መሐመድ የተላከው የፈጣሪን ምህረት ለዓለም ለማሳየት ነው፡፡ ነገር ግን ወታደራዊ አምባገነን በመሆን ጥቃትን ይፈፅም፣ ይገድል እና ለግዛቱ የሚሆን የዝርፍያ ገንዘብ ይወስድ ነበር፡፡ ይህ ምህረትን ሊያሳይ የሚችለው እንዴት ሆኖ ነው?

 

በቁርአን ውስጥ የተገለጠው አምላክ፣ አላህ አፍቃሪ አባት አይደለም፡፡ ሰዎችን በተሳሳተ መምራት መንገድ ይፈልጋል (ሱራ 6፡39፣ 126)፡፡ በእርሱ ወደ ተሳሳተ መንገድ የተመሩትን አይረዳቸውም (ሱራ 30፡29)፡፡ ገሃነምንም ለመሙላት ይቀምባቸዋል (ሱራ 32፡13)፡፡

 

እስልምና በሴቶች ላይ፣ ሙስሊም ባልሆኑት ላይ፣ በክርስቲያኖች ላይ እና በተለይም ደግሞ በአይሁዶች ላይ አድሎን በማድረግ የተሞላ ነው፡፡ ጥላቻ የኃይማኖቱ አካል ነው፡፡

 

የእኔ ልዩ የጥናት መስክ የሆነው የእስልምና ታሪክ የደም ወንዝ በመባል ብቻ ነው ሊገለፅ የሚችለው፡፡

 

አደገኛ ጥያቄዎች

 

በመጨረሻም በዩኒቨርሲቲ ካሉት ተማሪዎቼ ጋር እምነቱን እና ቁርአንን ጥያቄ ውስጥ የማስገባት ነጥብ ላይ ደረስኩኝ፡፡ አንዳንዶቹ የሽብርተኛ ቡድኖች አባላት ስለነበሩ በቁጣ ተሞሉ፡ “እስልምናን ልትወነጅል አትችልም፡፡ ምን ነካህ? ልታስተምረን ይገባሃል፡፡ ከእስልና ጋር መስማማት አለብህ፡፡”

 

ዩኒቨርሲቲው ስለ ጉዳዩ ስለሰማ በታህሳስ 1991 ለስብሰባ ተጠራሁኝ፡፡ የስብሰባውን ጭብጥ ለማስረዳት ያህል እኔ በልቤ ውስጥ የነበረውን ነገር ነገርኳቸው፡ “ቁርአን ከሰማይ ወይንም ከአላህ ዘንድ የመጣ ነው ብዬ ለመናገር ከእንግዲህ ወዲህ ይከብደኛል፡፡ ይህ የእውነተኛው አምላክ መገለጥ ሊሆን አይችልም፡፡”

 

በነርሱ አመለካከት እነዚህ ታላቅ የክህደት ቃላት ነበሩ፡፡ በፊቴ ላይ ተፉብኝ፡፡ አንድ ሰው እንዲህ በማለት ሰደበኝ “አንተ ከሃዲ! አንተ ዲቃላ!” ዩኒቨርሲቲው እኔን ከስራ በማባረር የግብፅን ህቡዕ ፖሊስ ጠራ፡፡

 

ህቡዕ ፖሊሶች አፍነው ወሰዱኝ

 

ቀጥሎ ምን እንደተከሰተ ለማወቅ ቤተ ሰቦቼ እንዴት እንደኖሩ ምስሉን ማግኘት ይኖርባችኋል፡፡ አባቴ የሦስት ፎቆች ርዝማኔ ያለው ትልቅ መኖርያ ቤት ነበረው፡፡ ወላጆቼ፣ አራት ያገቡ ወንድሞቼ ከነ ቤተ ሰቦቻቸው፣ ያላገባ ወንድሜ እና እኔን ጨምሮ መላው ቤተሰቦቼ በዚህ ቤት ውስጥ እንኖር ነበር፡፡ ያገባች እህቴ ነበር ከባሏ ጋር መኖር ስላለባት ሌላ ቦታ ትኖር የነበረው፡፡

 

ቤቱ በብዙ አፓርትመንቶች የተከፈለ ስለነበር በምቾት ነበር ስንኖር የነበረው፡፡ በመጀመርያው ደረጃ ላይ የወላጆቼ አፓርትመንት እና እኔ ከመንድሜ ጋር ተጋርቼ የምኖርበት አፓርትመንት ነበሩ፡፡ ከእኛ በላይ በሚገኙት ደረጃዎች ላይ ደግሞ ሌሎቹ ወንድሞቼ ይኖሩ ነበር፡፡

 

ዩኒቨርሲቲው እኔን ባባረረበት ዕለት ማለዳ ዘጠኝ ሰዓት ላይ አባቴ የቤታችን በር ሲንኳኳ ሰማ፡፡ ከአስራ አምስት እስከ ሃያ የሚገመቱ የሩሲያ ክላሽ ጠብመንጃዎችን የታጠቁ ሰዎች ወደ ውስጥ ተንጋግተው ገቡ፡፡ የደንብ ልብስ ሳይሆን ማንኛውም ሰው የሚለብሰውን ነበር የለበሱት፡፡ ደረጃዎችን እየሮጡ ወደ ላይ በመውጣት ሰዎችን እየቀሰቀሱ እኔን ይፈልጉኝ ነበር፡፡ እንደዚያ በዝተው ወደ ውስጥ የገቡበት ምክንያት እኔን ከማግኘታቸው በፊት ሮጬ እንዳላመልጥ በማሰብ ይመስለኛል፡፡

 

ከመካከላቸው አንዱ በተኛሁበት አልጋዬ ላይ እኔን ከማግኘቱ በፊት ሁሉም እቤት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ሰዎቹ እየጎተቱ ሲወስዱኝ ወላጆቼ፣ ወንድሞቼ፣ ሚስቶቻቸው እና ልጆቻቸው በሙሉ ያለቅሱ ነበር፡፡ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ሁሉ የተፈጠረውን ግርግር ሰምተው ነበር፡፡

 

እስር ቤት ወደሚመሰል ቦታ ተወስጄ በአንዲት ክፍል ውስጥ እንድገባ ተደረግሁኝ፡፡ ሲነጋም ቤተ ሰቦቼ የደረሰብኝን ነገር ለማጣራት ሞከሩ፡፡ በቀጥታም ወደ ፖሊስ ጣብያ በመሄድ “ልጃችን የት ነው?” በማለት ጠየቁ፡፡ ነገር ግን እኔ ያለሁበትን ማወቅ የቻለ ሰው አልተገኘም፡፡

 

እኔ በግብፅ ህቡዕ ፖሊስ እጅ ነበርኩኝ፡

 

ወደ ማውጫው መመለሻ

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ