8. ሸሀዳን እንዴት መካድ ይቻላል?

ምዕራፍ 8

ሸሀዳን እንዴት መካድ ይቻላል?

በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የተጠቀሰት ጸሎቶች ሦስት ክፍሎች አሏቸው ፡፡ የሚሸፍኗቸውም

§  ከሸሀዳና ከመሐመድ ምሳሌዎች አርነት መውጣት

§  ከማታለል አርነት መውጣት

§  ከየበላይነት ስሜት አርነት መውጣት

ከሸሀዳና ከመሐመድ ምሳሌዎች አርነት መውጣት

ሙስሊሞች  ሸሀዳን በሚያነበንቡበት ጊዜ መሐመድ የአላህ መልዕክተኛ ነው ይላሉ ቁርአንንም እንደ አላህ ቃል አድርገው ይወስዳሉ፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ ቁርአን ስለመሐመድ የተናገረውን ሁሉ ይቀበላሉ ማለት ነው፡፡ የግድ ሊከተሏቸው የሚገቡ ምሳሌዎቹንም ጭምር ማለት ነው፡፡ መሐመድን ሊከተሉ የማይወዱ የሚያጋጥማቸውን  ሥቃይና እርግማንም ይጠብቃሉ፡፡ በመሐመድ የማያምኑና የማይከተሉትን መዋጋት ሥራቸው እንደሆነም ያምናሉ፡፡

 

 

አሉታዊ የሆኑት አንዳንድ የመሐመድ ምሳሌዎች የሚከተሉትን ይይዛል፡፡

§  የኃይል ጥቃትና ጦርነት

§  ነፍሰ ገዳይነት

§  ሌሎችን ባርያ ማድረግ

§  መበቀልና መቅጣት

§  ሴቶችን መጥላት

§  አይሁዶችን መጥላት

§  ስድብ

§  ማፈርና ሌሎችን ማሳፈር

§  ሌሎችን መናቅ

§  ማታለል

§  ለማጥቃት መነሳት

§  ራስን ማጽደቅ/ ለሰሩት ጥፋት ኃላፊነት አለመውሰድ

§  የበላይነት ስሜት

§  የእግዚአብሔርን  ባህርያት አዛብቶ መተርጎም

§  ሌሎችን ለመጨቆን መፍቀድ እና

§  አስገድዶ መድፈር

ሸሀዳን በማነብነብ ሙስሊሞች ቁርአን እና በሱና ስለ ክርስቶስና እና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገሯቸውን ነገሮች መቀበላቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ እነዚህ ደግሞ የሚያጠቃልሉት፡

§  የክርስቶስን በመስቀል ላይ መሞት መካድ

§  መስቀልን መጥላት

§  ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ የሚለውን መካድ( ይሄንን የሚያምኑም ሰዎችን መርገም)

§  አይሁዶችና ክርስቲያኖች ቅዱሳን መጻሕፍትን በርዘዋል ብሎ ማመን

§  ኢየሱስ ዳግመኛ ተመልሶ የሚመጣው ክርስትናን ለማጥፋትና ዓለም ሁሉ ለመሐመድ ሸሪኣ እንዲገዛ ለማስገደድ ነው ብሎ ማመን

አንድ ሰው እስልምናን በሚተውበት ጊዜ በሸሀዳ ላይ የተጠቀሱትን  ማለትም መሐመድን እንደ ነብይ መቀበልን  መተውና መካድን ያጠቃልላል፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ ቁርአን የእግዚአብሔር ቃል ነው ብሎ አለመቀበል ማለት ነው፡፡

መሐመድ እንደ መልዕክተኛ ያለው ቦታ በግልጽ ካልተካደ በቁርአን ውስጥ የሚገኙት እርግማኖች እና ማፈራርያዎች እንዲሁም መሐመድ ለክርስቶስ ሞት እና ለክርስቶስ ጌትነት የነበረው ተቃውሞ መንፈሳዊ መዋዠቅን ሊያስከትል ችላል፡፡ ይህም አንድን ሰው በቀላሉ የወረደ ማንነት እንዲኖረው ሊያደርግ ይችላል፡፡ ከዚህም የተነሳ በቀላሉ ሊጎዳ ስለሚችል እንደ ክርስቶስ ተካታይ በእምነት የመከተል ችግር ያጋጥመዋል፡፡

 

ጸሎቶች

በመሐመድ ሕይወት የተገለጡትን ትምህርቶችና የሐሰት መገዛት እክዳለሁ፡፡

መሐመድ የአምላክ መልዕክተኛ ነው የሚለውን የውሸት እምነት አልቀበልም፡፡ እክደዋለሁም፡፡

ቁርአን የእግዚአብሔር ቃል ነው የሚለውን አነጋገር እክዳለሁ፡፡

ማንኛውንም ሸሀዳን ማነብነብ አግባብ ነው ብዬ አልቀበልም፡፡ እክደዋለሁም ፡፡

አል ፋቲሃ አይሁዶች ከእግዚአብሔር ቁጣ በታች ናቸው፣ ክርስቲያኖችም ከሀዲዎች ናቸው የሚለውን አስተምህሮ እክዳለሁ፡፡

አይሁዶችን መጥላትን እክዳለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በርዘውታል የሚባለውን አባባል አልቀበልም፡፡

እግዚአብሔር ኤሁዳውያንን ጥሏቸዋል የሚለውን አመለካከት እክዳለሁ፡፡

ቁርአንን ማነብነብና በሕይወቴ ላይ ስልጣን አለው የሚለውን አባባል እክዳለሁ፡፡

መሐመድን እንደ ምሳሌ በመቁጠር የሚደረግ ማንኛውንም የሐሰት አምልኮ እክዳለሁ፡፡

መሐመድ እግዚአብሔርን አስመልክቶ ያመጣውን የሐሰት ትምህርቶች እክዳለሁ፡፡ በቁራኑ ላይ የተገለጠውን አላህ እግዚአብሔር ነው የሚለውን አባባል እክዳለሁ፡፡

በተወለድኩ ጊዜ ለእስልምናና ለዘር ዘሮቼ የተሰጠሁበትን መሰጠት እክዳለሁ፡፡

የመሐመድን ምሳሌዎች ተከተል የሚለውን አስተሳሰብ እክዳለሁ፡፡

የኃይል ጥቃትን ፣ሌሎችን ዝቅ አድርጎ ማየትን፣ ጥላቻን፣ በሴቶች ያለአግባብ መጠቀምን፣ ሌብነትን፣ መሐመድ የፈጸማቸውን ሁሉንም ኃጢአቶች እቃወማለሁ፡፡ እክዳለሁ፡፡

በክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑቱ ከኩነኔ ነፃ መሆነቸውን፤ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከማንኛውም አሳፋሪ በደል ነፃ ስላወጣኝ ማንኛውንም አሳፋሪ ነገርን አልቀበልም፡፡ ደግሞም እክደዋለሁ፡፡

በሙስሊሞች የሚነገር ማንኛውንም የፍርሃት ንግግር አልቀበልም ደግሞም እክደዋለሁ፡፡ በሙስሊሞች ዛቻ የተነሳ በፍርሃት ውስጥ ለወደቁት እግዚአብሔር ይቅርታ እንዲያደርግላቸው፣ በሁሉም ነገራቸው በእግዚአብሔር መታመንን ምርጫቸው እንዲያደርጉ እጸልይላቸዋለሁ፡፡

እግዚአብሔራዊ ባልሆነው ማንኛውም ድርጊቴ ይቅርታ እንዲያደርግልኝ መሐመድንም የአላህ መልዕክተኛ ነው ብዬ በመከተሌ እግዚአብሔርን ምህረት እጠይቃለሁ፡፡

ኢየሱስ ዳግመኛ ወደ ምድር በሚመጣበት ጊዜ በምድር ላይ የሚኖሩ ሁሉም ሕዝቦች የመሐመድን ሸሪኣ እንዲቀበሉ ያስገድዳቸዋል የሚለውን የስድብ ንግግር እቃወማለሁ ፡፡ ደግሞም እክዳለሁ፡፡

ኢየሱስን ብቻ ለመከተል ምርጫዬ አድርጌአለሁ፡፡

ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን፣ ለኃጢአቴ በመስቀል ላይ መሞቱን፣ ለኔ ደህንነት ሲል ከሞት መነሳቱን አምናለሁ፡፡ ስለ ክርስቶስ መስቀል እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡ የኔን መስቀል ወስዶ እንድከተለው ስላደረገኝ፤

ክርስቶስ የሁሉም ጌታ መሆኑን አምናለሁ፡፡ በሰማይና በምድር ላይ ገዢ ነው፡፡ የሕይወቴ ጌታ ነው፡፡ በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ዳግመኛ እንደሚመጣ አምናለሁ፡፡ እንድንበት ዘንድ ከሰማይ በታች የተሰጠ ከኢየሱስ ሌላ ስም እንደሌለ አምናለሁ፡፡

አባቴ እግዚአብሔር አዲስን ልብ እንዲሰጠኝ ወደ ሕይወቴ እጋብዘዋለሁ፡፡ እርሱም የክርስቶስ ልብ ነው፡፡ በምናገረውና በማደርገው ሁሉ ይመራኝ ዘንድ፤

ሁሉንም የሐሰተኛ አምልኮዎች እቃወማለሁ፡፡ ህያው አምላክን ለማምለክ ማንነቴን አሰጣለሁ፡፡ አብ፣ ወልድና መንፈስቅዱስን፡፡

ከመታለል አርነት መውጣት

በኢስላሚክ ጅሃድ ላይ በመቃወም ተናግረዋል ተብለው በኢንዶኔዢያ ወህኒ ቤት በሐሰተኛ ክስ ታስረው የነበሩት መጋቢ ዳምኒክ ስለ እውነት እንዲህ ብለዋል፡፡

የቱንም ያህል እውነትን ማግኘት አስቸጋሪና ውድ ቢሆንም ሌላ ምርጫ የለንም፡፡ እውነትን ፍለጋ   ሊከፈል የተገባውን ውድ ዋጋ ሁሉ እንከፍላለን፡፡ ሊኖረን የሚገባ ምርጫ ካለ ደህና ሁኝ እውነት የሚል ይሆናል፡፡ የእውነት ወዳጆች እንደ ብረት የጠነከረ ነገር ሊኖራቸው እንደዚሁም ንጹህና ግልጽ የሆነ ልብ ያላቸው ናቸው (እንደ ብርጭቆ)፡፡ እንደሚታወቀው የብረት ምሰሶ ጠንካራ ነገር ነው፡፡ ሊታጠፍ የሚችልም አይደለም፡፡ የሚጸናና የማይለወጥም ነው፡፡

እንደ ብርጭቆ የሆነ ልብ ከተደበቀ ማንነት የጸዳና ንጹህ ማንነት ያለው ነው፡፡ በብርጭቆው እንደሚታየው እውነት ወዳጆች ስሜታዊ ናቸው፡፡ በዓለም ላይ ስላለው የፍትህ መዛባትና የሐሰት መንገስ በቀላሉ ሊሰበሩ የሚችሉ ናቸው፡፡  የልብ መሰበር የድካም ምልክት ተደርጎ መቆጠር የለበትም፡፡ ነገር ግን የጥንካሬና የኃይል ምልክት ነው፡፡ ጠንካራ ፈቃድ ያለውና የተሳለ አንደበት ያለው ነው፡፡ በውሸተኞች መካከልና በዙርያው ባሉት ሁሉ ላይ በግልጽና በድፍረት መናገር ይችላል፡፡ ልቡ ዝም ሊል አይችልም፡፡ ፍትህ በሚጣመምበት ጊዜ መታገስ ስለማይችል ፊት ለፊት ይጋፈጣል፡፡

እግዚአብሔር እውነት የመሆኑ እውነታ ከእርሱ ጋር ወደ ሕብረት ለመግባት ለኛ መሰረታዊ ነገር ነው፡፡

እግዚአብሔር በሕብረት ያምናል፡፡ ከሰው ልጆች ጋር ግንኙነትን እንዲኖረው መስመሩንም ዘርግቷል፡፡

አብርሃም፡

ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘላለም ኪዳን አቆማለሁ፡፡ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምልክ እሆን ዘንድ ፡፡ በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር የከንዓን ምድር ሁሉ ለዘላለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፤ አምላክም እሆናቸዋለሁ፡፡” (ዘፍ 17 7-8)

ዳዊት

ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ ለባርያዬም ለዳዊት ዘርህን ለዘላለም አዘጋጃለሁ፡፡ ዙፋንህንም ለልጅ ልጅ እመሰርታለሁ፡፡ (መዝ 893-4)

እግዚአብሔር በግንኝነቱ የማይለወጥና ታማኝ ነው፡፡ ሁልጊዜ ቃሉን ይጠብቃል፡፡

ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?” (ዘኁ 2319)

እግዚአብሔርን አመስግኑ ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም ነውናመዝ (1361)

[ስለ እስራኤላውያን ሲናገር] “…በምርጫ በኩል ግን ስለ አባቶች ተወዳጆች ናቸው፤ እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና” (ሮሜ 1128-29)

“…ለተመረጡት እምነት እንዲሆንላቸው በዘላለምም ሕይወት ተስፋ እንደ አምልኮት ያለውን እውነት የማይዋሽ እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት ተስፋ ሰጠ፡፡” (ቲቶ 12)

ስለዚህም እግዚአብሔር የተስፋውን ቃል ለሚወርሱ ፈቃዱ እንደማይለወጥ አብልጦ ሊያሳያቸው ስለ ፈቀደ እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት ይሆንልን ዘንድ በመሐላ በመካከል ገባ፤ ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን እርሱም እርግጥና ጽኑ የሆነ ወደ መጋረጃውም ውስጥ የገባ ነው፡፡ (ዕብ 6 17-19) እግዚአብሔር ግን የታመነ ነው፡፡ ለእናንተም የሚነገረው ቃላችን አዎንና አይደለም አይሆንም፡፡ በእኛ ማለት በእኔና በሰልዋኖስ በጢሞቴዎስም በመካከላችሁ የተሰበከ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አዎንና አይደለም አልነበረም ነገር ግን በእርሱ አዎን ሆኗል፡፡ እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ  አዎን ማለት በእርሱ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ስለክብሩ በእኛ የሚነገረው አሜን በእርሱ ደግሞ ነው፡፡” (2ቆሮ 118-20)

በቁርአን ግን ይሄ የአላህ ስብእና አይደለም፡፡

ከመልክተኛ ማንኛውንም ለነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ በሌላ አልላክንም አላህም የሚሻውን ያጠማል፤ የሚሳንም ያቀናል፤ እርሱም አሸናፊው ጥበብ ነው፡፡ (144)

እውነተኛው የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር እርሱን እንድንመስለው ይፈልጋል፡፡

እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲህ በላቸው፦ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ።” (ሌዋ 191-2)

የእግዚአብሔርን ቅድስና ከምንገልጥባቸው መንገዶች መካከል አንዱ እውነተኛ በመሆን እና በእውነት በመኖር ነው ምክንያቱም እግዚአብሔር እውነት ነውና፡፡ ሰይጣን ውሸትን በልባችን ውስጥ መጨመር ያስደስተዋል፡፡ የእግዚአብሔር እውነት ግን ይጠብቀናል፡፡

ምሕረትህ በዓይኔ ፊት ነውና፥ በእውነትህም ተመላለስሁ።” (መዝ 263)

በእጅህ ነፍሴን እሰጣለሁ የእውነት አምላክ አቤቱ፥ ተቤዥተኸኛል።” (መዝ 315)

አቤቱ፥ አንተ ምሕረትህን ከእኔ አታርቅ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ።” (መዝ 4011)

እውነት ያነፃናል

እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ።

እነሆ፥ እውነትን ወደድህ የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ። በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነፃማለሁ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ።” (515-7)

ኢየሱስ በእውነት የተሞላ ነው

ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።” (ዮሃ 114)

በእውነት እንድንሄድና እንድንኖር ተጠርተናል

እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል።” (ዮሃ 321)

በወንጌላት ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ 78 ጊዜ እውነት እላችኋለሁ በማለት ተናግሯል፡፡ በእውነት ብቻ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንደምንችል ነግሮናል፡፡

እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።” (ዮሃ 424)

ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” (ዮሃ 146)

ጳውሎስም ውሸት በመናገርና ክርስቶስን በመከተል መካከል ስላለው አለመጣጣም ይናገራል

ይኸውም፥ ለበደለኞችና ለማይታዘዙ፥ ለዓመጸኞችና ለኃጢአተኞች፥ ቅድስና ለሌላቸውና ለርኵሳን፥ አባትና እናትን ለሚገድሉ፥ ለነፍሰ ገዳዮችና ለሴሰኞች፥ ከወንድ ጋርም ለሚተኙ፥ በሰዎችም ለሚነግዱ፥ ለውሸተኞችም በውሸትም ለሚምሉ፥ የብሩክ እግዚአብሔርንም ክብር እንደሚገልጥ ለእኔ አደራ እንደ ተሰጠኝ ወንጌል የሆነውን ደኅና ትምህርት ለሚቃወም ለሌላ ነገር ሁሉ ሕግ እንደ ተሰራ እንጂ ለጻድቅ እንዳልተሰራ ሲያውቅ ነው።

 

 

የባሕል ጉዳይ

እንደ እስልምና ከሆነ ውሸት በተወሰኑ ሁኔታዎች ውስጥ ተፈቅዷል፡፡ በቁርአን ውስጥ አምላክ ሰዎችን ያታልላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ውሸት ግዴታ ይሆናል፡፡ (ማታለልና ታቅያ በሚል ርዕስ ላይ የተደረገውን ትንተና The Third Choice በሚለው መጽሐፍ ላይ ከገጽ 56 ጀምሮ ይመልከቱ)፡፡

የሸሪኣ ህግ የሚደነግጋቸው የውሸት ዓይነቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡ በጦርነት ጊዜ መዋሸት፣ ባል ሚስቱን መዋሸት፣ ራስን ለመጠበቅ መዋሸት፣ ኡማውን ለመጠበቅ መዋሸት፣ ሙስሊሞች በአደጋ ውስጥ እንዳሉ ካመኑ ራስን የመጠበቅ ውሸት (ታቅያ)፡፡

በእስልምና ኃይማኖታችሁን መካድ የተፈቀደ ነው፡፡ ነገር ግን ክርስቲያን በንዲህ ዓይነት መንገድ መኖር አይችልም፡

ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።” (ማቴ 1028-33)

ኢየሱስ ንግግራችሁ አዎን ከሆነአዎንበሉ ንግግራችሁ ደግሞ አይደለም ከሆነአይደለምበሉ ብሏል፡፡

 

 

ጸሎቶችና አዋጆች

አባት ሆይ አንድ ነገር አውቃለሁ አንተ የእውነት አምላክ ነህ፡፡ በጨለማው ምሽት ላይ ብርሃንህን አብርተሃል፡፡ ዛሬ በጨለማ ውስጥ ሳይሆን በብርሃንህ ውስጥ ለማደር መርጫለሁ፡፡

እባክህን የዋሸኋቸውን ውሸቶች ሁሉ ይቅር ትል ዘንድ እማጸንሀለሁ፡፡ ምቾት ያለበትንና ቀላሉን መንገድ መርጫለሁ ትክክለኛውን ግን አይደለም፡፡ በከናፍርቶቼ የበደልትን በደል ሁሉ ይቅርበለኝ፡፡ በእውነትህ የምደሰትበትን ልብ ስጠኝ፡፡ እውነትን ለሌሎች የሚናገር አንደብትንም ስጠኝ፡፡

ውሸትን የማስወግድበትና በእውነት የምጽናናበትን ብርታት ስጠኝ፡፡

በእየለቱ ኑሮዬ የምዋሸውን ውሸት ዛሬ አስወግዳለሁ ድግሞም እክደዋለሁ፡፡

ውሸትን የሚያበረታታውን የሙስሊሞችን አስተምህሮ አስወግዳለሁ ታቂያንም ጨምሮ፡፡ ከማንኛውም ውሸትና ማታላል ራሴን ዞር አደርጋለሁ በእውነት ለመኖር መርጫለሁ፡፡

ዋስትናዬ ያለው ባንተ መሆኑን አውጃለሁ እውነትም አርነት ያወጣኛል፡፡

የሰማይ አባት ሆይ በእውነትህ ብርሃን እንዴት መመላለስ እንዳለብኝ አሳየኝ፡፡ የምናገራቸውንም ቃሎች ስጠኝ በእውነትህ ላይ እንድራመድም መንገዱን አሳየኝ፡፡

 

ከየበላይነት አስተሳሰብ አርነት መውጣትና መብት መስጠት

በእስልምና የበላይ በመሆንየተሻለው ማነውበሚለው ላይ  ላይ ልዩ አጽንዖት ይሰጠል፡፡ ፡፡ ቁርአን ሙስሊሞች ሙስሊም ካልሆኑት የተሻሉ ናቸው ብሎ ያስተምራል፡፡

ለሰዎች ከተገለጸች ሕዝብ ሁሉ በላጭ ኾናችሁ በጽድቅ ነገር ታዛላችሁ፤ ከመጥፎም ነገር ታዛላችሁ፤ በአላህም (አንድነት) ታምናላችሁ፡፡ የመጽሐፉም ሰዎች ባመኑ ኖሮ ለነርሱ የተሻለ በኾነ ነበር፡፡ ከነርሱ አማኞች አሉ፡፡ አብዛኞቻቸው ግን አመጸኞች ናቸው፡፡” (310)

 

እስልምና በሌሎች ኃማኖቶች ሁሉ ላይ የበላይ ሆኖ መግዛት ይፈልጋል፡

 

እርሱ መልክተኛውን በመሪ መጽሐፍና በእውነተኛ ኃይማኖት በኃይማኖት ሁሉ ላይ ሊያልቀው የላከ ነው፡፡ መስካሪም በአላህ በቃ፡፡” (4828)

 

በመሐመድ ብዙ ሀዲሶችም  የበላይ ስለመሆን ታላቅ አጽንዖት ተሰጥቷል፡፡

የእስልምና ኃይማኖት በአረብ ባህል ውስጥ ትልቅ ተፅዕኖ ፈጥሯል፡፡ ይሄም 1000 ዓመት በላይ ቅርጽ ይዞ እንዲሄድ አድርጓል፡፡  በአረብ ባህልክብር  “ሀፍረትበጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ ሰዎች የበታች ሆኖ መታየት እጅግ ያሳፍራቸዋል፡፡  አንድ ግጭት በሚኖርበት ጊዜ ሌላውን ዝቅ አድርጎ በማየት ሌሎችን በማጥቃት እርካታ የማግኘት አዝማምያ ይታያል፡፡

አንድ ሰው እስልምናን ትቶ በመውጣት ክርስቶስን ለመከተል የሚወስን ከሆነ  ሰዎች በሌሎች ላይ የበላይ በመሆን በዚም እርካታን ለማግኘት ጥረት የሚያደርጉበትን የስሜታዊነት ንጽረተ ዓለም መካድ ይገባቸዋል፡፡

ከዚህ ጨቋኝ ከሆነ ንጽረተ ዓለም ነፃ የመውጫው መንገድ የክርስቶስ ምሳሌነት ነው፡፡ ጳውሎስ ለፊልጵሲዩስ ሰዎች በላከው ሁለተኛ መልዕክት ላይ ይህ ውብ በሆነ ሁኔታ ተገለጾዋል፡

በክርስቶስም አንዳች ምክር ቢሆን፥ የፍቅር መጽናናት ቢሆን፥ የመንፈስ ኅብረት ቢሆን፥ ምሕረትና ርኅራኄ ቢሆኑ፥ ደስታዬን ፈጽሙልኝ፤ በአንድ አሳብ ተስማሙ፥ አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤ ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ። በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው። (ፊል 2)

 

ከመካከላቸው ማን የተሸለ እንደሆነ በኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መካከል በተለያዩ ጊዜያት ጥያቄ ይነሳ ነበር፡፡ በኢየሱስ መንግስት ውስጥ የክብር ስፍራ ሊኖረው የሚችለው ማን እንደሆነ ማወቅ ይፈልጉ ነበር፡፡

የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ወደ እርሱ ቀርበው። መምህር ሆይ፥ የምንለምንህን ሁሉ እንድታደርግልን እንወዳለን አሉት። እርሱም፦ ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው። እርሱም፦ በክብርህ ጊዜ አንዳችን በቀኝ አንዳችንም በግራህ መቀመጥን ስጠን አሉት። ኢየሱስ ግን፦ የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ፥ እኔ የምጠመቀውንስ ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን? አላቸው። እርሱም፦ እንችላለን አሉት። ኢየሱስም፦ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፥ እኔ የምጠመቀውንም ጥምቀት ትጠመቃላችሁ፤ በቀኝና በግራ መቀመጥ ግን ለተዘጋጀላቸው ነው እንጂ የምሰጥ እኔ አይደለሁም አላቸው። አሥሩም ሰምተው በያዕቆብና በዮሐንስ ይቈጡ ጀመር። ኢየሱስም ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ የአሕዛብ አለቆች ተብሎ የምታስቡት እንዲገዙአቸው ታላላቆቻቸውም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ። በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥ ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የሁሉ ባሪያ ይሁን፤ እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።” (ማር 1035-45)

ኢየሱስ እዚህ ቦታ ላይ አሕዛብ ብሎ የሚጠራው ሁሉንም ሕዝቦች ነው፡፡ የተፈላጊነት ስሜት እንዲሰማን መሻት ዓለም አቀፋዊ የሆነ የሰዎች ሁሉ አባዜ ነው፡፡ ልክ እንደ ያዕቆብና ዮሃንስ በመላው ዓለም ላይ የሚገኙ ሰዎች የተሻለውን መቀመጫ ወይንም ደግሞ የተሻለውን ክብር ይፈልጋሉ፡፡ ኢየሱስ ለዚህ መሻት መልስን የሰጠው ደቀ መዛሙርቱ በእውነት ሊከተሉት የሚፈልጉ ከሆነ ሌሎችን እንዴት ማገልገል እንደሚችሉ ማወቅ እንደሚያሻቸው በመንገር ነበር፡፡ በአንድ ልዩ መንገድ ኢየሱስ ይህ ተግባራዊ ሊሆን እንዴት እንደሚችል አሳይቷል፡፡ በዝያን ዘመን በነበሩ ሕዝቦች ዘንድ እንደ አሳፋሪ አሟሟት ለሚቆጠረው የመስቀል ሞት ራሱን አሳልፎ አስኪሰጥ ድረስ  “ራሱን ባዶ አደረገ” (ፊል 27)፡፡

በሌሎች ላይ የመሰልጠን ፍላጎት የሰው ልጆች ትልቅ ወጥመድ ነው፡፡ በኤደን ገነት እባብ ሄዋንን የፈተናት እንደዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ይዞ ነው፡፡እንደ እግዚአብሔር ትሆናላችሁበማለት (ዘፍ 34) በዚህ መሰረት ሄዋን እባቡ ያላትን መሆን ፈለገች፡፡ ከዚህም የተነሳ በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ ችግርና ስቃይ እንዲፈጠር ምክንያት ሆነ፡፡ ይሄ ደግሞ የሆነበት ምክንያቱ በሌሎች ላይ የበላይ ለመሆን ካለ ጥልቅ ፍላጎት የተነሳ ነው፡፡

ከዚህ አንፃር የኢየሱስ አስተሳሰብ በእጅጉ የተለየ ነው፡፡ አገልጋይ መሆንን መረጠ፡፡ የበላይ መሆንን ግን አይደለም፡፡ ማንንም አልገደለም፡፡ ይልቁንም ለሌሎች ቤዛ በመሆን መስዋእት ሆነ እንጂ፡፡ እውነተኛ የክርስቶስ ተከታይም ማድረግ የሚገባው ተመሳሳይ ነገር ነው፡፡ ማንም ሰው በሌሎች ላይ የበላይ ሆኖ በመታየት ሊያገኝ የሚችለው አንዳች ደስታ የለም፡፡ እውነተኛ የክርስቶስ ተከታዮች ሌሎች በሚያስቡት ነገር ፍራቻም ሆነ ሀፍረት አይሰማቸውም፡፡

በሌሎች ላይ የበላይ የመሆን ፍላጎት አደገኛ ገጽታ እንዳለው የምንማረው በሉቃስ 1511-32 ላይ ከተጠቀሰው የአባካኙ ልጅ ታሪክ ነው፡፡መልካምልጅ የተባለው የበላይነት ስሜት ስለተሰማው አባቱ ጠፍቶ ለተገኘው ልጅ ባዘጋጀው የደስታ ግብዣ ላይ ለመገኘት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ በዚህም ምክንያት በአባቱ ተገስጾ ነበር፡፡ ወደ እውነተኛ  ስኬት የሚወስደው መንገድ በእግዚአብሔር እይታ በሌሎች ላይ ጌታ መሆን ሳይሆን ሌሎችን ዝቅ ብሎ ማገልገል ነው፡፡

ጸሎቶችና አዋጆች

አባት ሆይ ድንቅ አድርገህ ስለፈጠርከኝ አመሰግንሀለሁ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የፈጠርከኝ አንተ ስለሆንክ ነው፡፡

ስለወደድከኝና የአንተ ስላደረግከኝ አመሰግንሀለሁ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን የምከተልበትን እድል ስለሰጠኸኝ አመሰግንሀለሁ፡፡

የበላይ የመሆንን ፍላጎት በማስተናገዴ ምህረትን አድርግልኝ፡፡ ከሌሎች የተሻለ ሆኖ ለመገኘት ፍላጎቴ በመገዛቴም ይቅር በለኝ፤  እንደ ማንኛውም ሰው ኃጢአተኛ መሆኔን አውቃለሁ፡፡ ያለ አንተም አንዳች ማድረግ አልችልም፡፡

የኋላ ታሪኬን በምመለከትበት ጊዜም ሆነ አሁን ባለሁበት ሁኔታ በቡድን ውስጥም ባለኝ ግንኙነት የበላይ ለመሆን ለነበረኝ ፍላጎት ይቅር በለኝ፤ እኔም እክደዋለሁ፡፡ ሁሉም ሰዎች በአንተ ፊት እኩል መሆናቸውን አምናለሁ፡፡

ሌሎችን ዝቅ የሚያደርግ ንግግርን በመናገሬ ይቅርታ አድርግልኝ፡፡ ለነዚህ ቃላቶቼ ምህረትን እጠይቃለሁ፡፡

በዘራቸው፣ በፆታቸው፣ በሀብታቸውና በትምህርታቸው ምክንያት ሌሎችን ዝቅ አድርጎ ማየትን እቃወማለሁ፡፡


በፊትህ
መገኘት የቻልኩት በጸጋህ ብቻ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ በሰው ልጆች ላይ ሊደረግ ካለሁ ከማንኛውም ፍርድ እራሴን እለያለሁ፡፡ ያዳንከኝን አንተን ብቻ እመለከታለሁ፡፡

ጻድቆች የበላይ ናቸው የሚለውን የሙስሊሞች አስተምህሮ እክዳለሁ፡፡ ሙስሊም መሆን ስኬታማ ያደርጋል፣ ሙስሎሞች  የበላይ ሕዝቦች ናቸው የሚለውን እክዳለሁ፡፡

ወንዶች ከሴቶች የበላይ ናቸው የሚለውን አስተሳሰብ አልቀበልም፡፡ ደግሞም እክዳለሁ፡፡

የሰማዩ አባት እግዚአብሔር ሆይ ከነበረኝ ማንኛውም የበላይ የመሆን አስተሳሰብ እመለሳለሁ፡፡ አንተንም ለማገልገል መርጫለሁ፡፡

ጌታ ሆይ በሌሎች ስኬት ለመደሰት መርጫለሁ፡፡ በሌሎች ላይ መቅናትና ጥላቻን አልቀበልም ደግሞም እክደወለሁ፡፡

ጌታ ሆይ በፊትህ ምን ዓይነት ሰው ስለመሆኔ ጤናማና ትክክለኛውን ፍርድ ስጠኝ፤ እንዴት እንደምታየኝ እውነቱን አስተምህረኝ፡፡ አንተ የምትፈልገው ዓይነት ሰው እንድሆንልህ እርዳኝ፡፡

 

ዋቢ መጻሕፍት/ Bibliography

Bernard, J.H. 1928. A critical and exegetical on the Gospel according to John. 2 vols. Edinburgh: T&T Clark.

Carson, D.A. 1991. The Gospel according to John. Leicester, England: Inter-Varsity press.

Gibson, Noel and Phyl. 1987. Evicting demonic squatters and breaking bondages. Drummoyne, NSW: Freedom in Christ Ministries Trust. (An earlier edition of Evicting demonic intruders.)

Houlden, J.H. 1970. Paul’s letters from prison: Philipians, Colossians, Philemon and Ephesians. Harmondsworth, Middlesex: Penguin.

Kreider, Alan. 1995. Worship and Evangelism in pre-Chrestendom. Alcuin/GROW Joint Liturgical Studies, 32. Cambridge: Grove Books Ltd.

 

Muir, William. 1861. The life of Mahomet. London: Smith, Elder and Co.