‹በላቸው› - የሚለው የተምታታ አባባል

የተዘበራረቀበት የቁርአን ጸሐፊ!

Jochen Katz

ርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

ቁርአን 2.97 የሚከተለውን ዓረፍተ ነገር ያቀርብልናል፡- ‹በላቸው ለጂብሪል (ለገብሬል) ጠላት የኾነ ሰው (በቁጭት ይሙት) በላቸው፣ እርሱ (ቁርአኑን) ከበፊቱ ለነበሩት (መጻሕፍት) አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና፡፡ቁርአን 297፡፡

ይህንን ጥቅስ በመጀመሪያ ያነበበ ሰው በአዕምሮው ውስጥ የተለያዩ ጥያቄዎች ይፈጠርበታል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ሊኖሩበት ይችላሉ፡-

1. ‹በላቸውተብሎ የተነገረው ማነው? ከዚያ ቀጥሎስ ያለውን መልእክት መናገር ወይንም ማወጅ ያለበት እርሱ ማነው?

2. ‹በላቸውከተባለው ቃል ቀጥሎ፣ መልእክቱ እየተነገረ ያለው ለማነው?

3. የገብሬል ጠላት ለመሆን የሚፈልገው እርሱ ማነው? እንዲሁም እነዚህን የገብሬል ጠላቶች የሆኑትን ቁርአን ለምን ይናገራቸዋል?

4. ቁጥሩ በመጀመሪያ አንድ ሰውን ወይንም የሰዎች ቡድኖችን ወስኗል፡፡ እነሱምለገብሬል ጠላት የሆነ ሰውወይንምሰዎችን ቀጥሎ ግን ወደ ሌላ ነገር ተለወጠ፡፡ እነዚያ ሰዎችስ? እነሱ ምን ማድረግ አለባቸው ወይንም በእነሱ ላይ ምንድነው የሚሆነው ነገር? ዓረፍተ ነገሩ ሳይሟላ እንደተጀመረ ተትቷል፡፡ የዓረፍተ ነገሩ ባለቤት አሁንም በአየር ላይ እንደተንጠለጠለ ነው፣ እናም በእሱ ላይ ምንም ነገር አልሆነም፡፡

5. እርሱአውርዶታልየተባለው፣ እርሱ ማነው? ‹እርሱየሚለው ተውላጠ ስም የሚያመለክተው ለገብሬል ነውን? ወይንስ በዚህ ጥቅስ ውስጥ ገና ስላልተጠቀሰው ሰው ወይንስ ስለአንድ ሌላ ነገር ነውን የሚያመለክተው?

6. ‹የወረደውየተባለውስ ነገር እርሱ ምንድነው?

7. ‹በልብህ ላይበሚለውናነገሩ የወረደበትየተጠቀሰው የሚጠቁመው ስለማን ልብ ነው?

እነዚህ ጥያቄዎች የቁርአን ተርጓሚዎች እንደዚህ ስላስቀመጧቸው የተነሱ አይደሉም፡፡ በሌላ ጎኑ ለአረብኛው በጣም በቀረበ በአርበሪ ትርጉምም እንኳን የዚህ ጥቅስ የእንግሊዝኛ ትርጉም ልክ እንደ አረብኛው ግልፅ ያልሆነና የማያረካ ነው፡፡ ስለዚህም ብዙዎቹ ተርጓሚዎች በእርሱ ላይ ቃላትን ጨምረውበታል (ይህም በቅንፍ ወይንም ያለቅንፍ ጭምር ነው) ይህም ክፍሉን ወይንም ትርጉሙን ለማብራራት (?) ነው፡፡ የሚከተሉትን ልዩ ልዩ ትርጉሞች ከዚህ በታች እንመልከት ደማቆች የኔ ናቸው፡፡

 መሐመድ ሆይ በላቸውሰላም በእሱ ላይ ይሁን› -- ‹በላቸው ለጂብሪል (ለገብሬል) ጠላት የኾነ ማንም ሰው (እርሱ በቁጭት ይሙት) በእርግጥ እርሱ በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶ አምጥቶታል (ይህን ቁርአን) ከእርሱ በፊቱ የመጡትን ለማረጋገጥ (ማለትም ቶታትን (ሕግን) እና ኢንጂልን (ወንጌልን) ለአማኞችም መሪና የደስታ ዜና› (Al-Hilali & Khan) ቁርአን 297፡፡

መሐመድ ሆይ ለሰው ልጆች በላቸው ለጂብሪል (ለገብሬል) ጠላት የኾነ ሰው ማነው! በአላህ ፈቃድ (ይህንን ቅዱስ ቃል) ለልብህ የገለጠው እሱ ነውና፣ ከእርሱ በፊት የተገለጡትን የሚያረጋግጥ ሆኖ፣ እንዲሁም ለአማኞች መሪና ብስራት ነው፡፡› (Pickthall) ቁርአን 2.97፡፡

መሐመድ ሆይ በላቸው ለጂብሪል (ለገብሬል) ጠላት የኾነ ማንም ሰው ማወቅ ያለበት በአላህ ትዕዛዝ ይህንን ቁርአን ለልብህ እንደገለፀው ነው፣ እሱም ከዚህ በፊት የነበሩትን ቅዱሳት መጻሕፍትን አረጋጋጭ ነው፣ እንዲሁም ለአማኞች መሪና የምስራች ዜና ነው› 2.97 (Malik)፡፡

(በአሕዛብ ነቢይ ላይ መገለጥን ባመጣው በገብርኤል ደስተኞች አልሆኑም 2.90)በላቸው፤ ለገብርኤል ጠላት የሆነው ማነው! በአላህ ፈቃድ ይህንን (ቁርአንን) ለአንተ ልብ የገለጠው እርሱ (እና ይህም መገለጥ) የቀደሙትን ቅዱሳን መጻሕፍት መለኮታዊ ምንጭ አረጋጋጭ ነው፡፡ እርሱም ለሚቀበሉት መሪና የምስራች ዜና ነው፡፡› 2.97፡፡ (Shabbir Ahmed, QXP)፡፡

በላቸው፣የገብርኤል ጠላት የነበረው ማነው፣ በእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱ በአንተ ልብና አዕምሮ ላይ አውርዶታል፣ በእጆቹ መካከል በማረጋገጥ እናም ለአማኞች መሪና የምስራች ዜና ነው፡፡› (Mohamed & Samira Ahmed, Literal Translation)::

በላቸው ለጂብሪል (ለገብሬል) ጠላት የኾነ ማንም ቢኖር፣ በእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱ ወደ ልብህ ውስጥ የላከው መሆኑን እወቅ፣ ያለውን ለማረጋገጥ እንዲሁም ለአማኞች መሪና የምስራች ዜና፡፡› (ProgressiveMuslims.org)::

በላቸው፣ ለገብርኤል ማንም ጠላት ቢሆን - በእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱ ነበር በልብህ ላይ ያወረደው፣ ከእርሱ በፊት የነበረውን ለማረጋገጥ እንዲሁም ለአማኞች መሪና የምስራች ዜና፡፡ (Arberry)

የሙስሊም ተንታኞች እና ተርጓሚዎች ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት ጥያቄዎች ውስጥ ጥያቄ አንድን ለመመለስ በጣም ተመሳሳይ ናቸው፣ እናምበላቸው!› የሚለው ትዕዛዝ የተነገረው ለመሐመድ ነው ይላሉ፡፡ ከዚያም የሚቀጥለውን እንዲያስታውስ ወይንም እንዲናገር የሚጠበቀው እሱ ነው፡፡

በጥያቄ አራት ላይ አንዳንድ አስተያየቶች፡-በእራሱ ቁጭት ይሙትየሚለውን (Al-Hilali & Khan) ትርጉም በአጠቃላይ ክፍሉ ላይ ሙሉ ሐረግን ጨምሮበታል፣ ይህምማንም የገብርኤል ጠላት ቢኖርየሚለው የቁጥሩ ክፍል ሙሉ ዓረፍተ ነገር ስላልሆነ በራሱ ምንም ስሜት የማይሰጥ ለመሆኑ ግልጥ የሆነ ማስረጃ ነው፡፡ (Malik) ደግሞማንም ሰው ማወቅ አለበትየሚለውን በንግግሩ የመጀመሪያና ሁለተኛ ክፍል መካከል ላይ ጨምሯል፣ ይህም ሁለቱን በተቻለ መጠን ለማገናኘት ነው፡፡ (Al-Hilali & Khan) እንዲሁም (Pickthall) መስተፃምር የሆነውንወይንም (ምክንያት) እንዲሆን ማለትም የሁለተኛው ክፍል ለመጀመሪያው ክፍል ምክንያትን እንዲሰጥ ለማድረግ አስበው ጨምረውበታል፡፡ ይሁን እንጂ አንድ ሰው ይህ ለምን እንደተደረገ ምክንያትን ሊጠይቅ ይችላል፡፡ የመጀመሪያው ዓረፍተ ነገር ከምክንያት ጋር በመያያዙ ብቻ ሙሉና ትርጉም ያለው ዓረፍተ ነገር ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱምበምክንያት እንዲደገፍ በመጀመሪያ ሙሉ ዓረፍተ ነገር መሆን ያስፈልገዋል፡፡ (Arberry) ጭረትን በመጠቀም እና የሐሳብ መቋረጥ መኖሩን በማሳየት በጣም ትክክል በሆነ መንገድ አቅርቦታል፡፡ ይሁን እንጂ ይህም ደግሞ ወደሚቀጥለው ችግር ይመራናል፡፡  

አምስተኛውና ስድስተኛው ጥያቄዎች፡-እሱየሚለው ቃል የሚናገረው ስለማነው? በአረብኛው ጽሑፍእሱየሚለው ቃል ለገብርኤል ወደ ኋላ ተመልሶ የሚጠቅስ ስለመሆኑ ወይንም በጥቅሱ ውስጥ ስላልተጠቀሰ ስሌላ ሰው ስለ መሆኑ ምንም ግልፅ አይደለም፡፡ እንዲሁም አንድ ሌላ ነገርም ግልፅ አይደለም፣ ያም እሱ ያወረደውእሱንነው ወይንስአንድ ነገርንነው፣ ማለትም ገብርኤልን ነው ያወረደው ወይንስ በጥቅሱ ውስጥ ያልተገለጠ ሌላ አንድ ነገርን ነው? ብዙዎቹ ተርጓሚዎች ይህንን ተውላጠ ስም ከቁርአን ጋር ያያይዙታል፣ በእርግጥም ይህ ምክንያታዊ አገማመት ነው፣ ነገር ግን አስፈላጊ መደምደሚያ አይደለም፡፡ ቁርአን እዚህ ላይ መጽሐፍን ወይንም ቅዱስ መጽሐፍትን አይደለም የሚጠቅሰውና፡፡

ከዚህ በላይ ያሉት ሁሉም ነጥቦች ቁርአን የስነ ጽሑፍ ውበት ተዓምራት እንዳለው የሚጠቁም ምንም ስሜትን በእርግጥ አይሰጡም፡፡ ይሁን እንጂ ግልፅ አለመሆን እና ምስጢር አንድ ነገር ሲሆን መሳሳት ማለት ደግሞ ሌላ ነገር ነው፡፡

ይህ ጥቅስ ትርጉመ ቢስና ግልፅ ብቻ ሳይሆን በሚናገረው ነገር ስህተት ነው፡፡ ምክንያቱም የሚጠቀመው የተሳሳተ የባለቤትነትን ተውላጠ ስም ነውና (ይህም ከዚህ በላይ ባሉት የተለያዩ ትርጉም ጥቅሶች ላይ ግልፅ ነው)፡፡ ጥያቄ ቁጥር ሰባትን ለመመለስ በሚሞከርበት ጊዜ ብቸኛ መደምደሚያ ሊሆን የሚችለው ነገር ቁርአን የስህተትን ዓረፍተ ነገር ሰርቷል ነው፡፡

በሙስሊም ተንታኞች መሰረት መሐመድን ወደዚህ ጥቅስ መገለጥ የመራው ታሪካዊው ዓውድ አይሁዶች እርሱ ነቢይ እንዳልነበረ የመናገራቸው ውንጀላ ነው፡፡ እርሱም እዚህ የተናገረው ቁርአን የመጣለት እነሱ በሚያውቁት በገብርኤል እንደሆነ ነው፡፡ (ከአይሁድ የመጣው ምላሽ ግን ያልተጠበቀ ነበር) ገብርኤል የጦርነትና የመከራ መልአክ እንደነበረና የአይሁድም ጠላት እንደነበረ በአይሁድ ቡድኑ ምላሽ ይሰጣል፣ ነገር ግን መገለጥን አመጣ የተባለው መልአኩ ሚካኤል ቢሆን ኖሮ መሐመድን ያምኑበት ነበር፣ ምክንያቱም ሚካኤል የእነሱ ጓደኛ፣ የሰላምና የምህረት መልአክ ነውና፡፡ ስለዚህም ይህ ጥቅስ ማለትም 2.97 ለመሐመድ የተሰጠው አይሁዶቹ ያሉትን ነገር ለመቃወምና ለማፍረስ ነበር፡፡  

ይሁን እንጂ መሐመድ በእነሱ ተቃውሞ በጣም ተሸብሮ ነበር፣ ስለዚህም አይሁዶችን ፀጥ ለማሰኘት የታቀደውን የመገለጡንም ቃላቶች እንኳን እንደሚገባ አላስቀመጣቸውም፡፡

የአይሁድ ቡድኑም ተቃውሞ፡- ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ መገለጥን አያመጣም ነበር፡፡ ስለዚህ እኛ አናምንህም ነበር፡፡ የመልሱም ዋናው ዓረፍተ ነገር ማለትም 2.97 ላይ የተሰጠው ለዚህ የአይሁዶች ተቃውሞ ነበር፡፡እርሱ (ቁርአኑን) ... በልብህ ላይ አውርዶታልና፡፡ነገር ግን ይህ የተቀናበረው ለራሱ ለመሐመድ ማረጋገጫ እንደሚሆን ተደርጎ ነበር፡፡ ማለትምመሐመድ እርግጠኛ ሁን እሱን በአላህ ፈቃድ በአንተ ልብ ላይ ያወረደው በእርግጥ ገብርኤል ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የቁጥሩ አጠቃላይ አመሰራረት በዚህ ብቻ አያበቃም፣ ይህ ማረጋገጫ ወይንም ማፅናኛ ለመሐመድ የተሰጠው ለተቃዋሚዎቹ እና ገብርኤል ጠላታችን ነው በማለት ለተናገሩት እርሱ እንዲናገረው በትዕዛዝ መልክ ሆኖ ነው፡፡

እንግዲህ የቁርአን ጸሐፊ እጅግ በጣም መጥፎ በሆነ ሁኔታ የተምታታበት እዚያ ነጥብ ላይ ነው ምክንያቱም ተውላጠ ስሙን ሳይለውጥ፣ (ለእነሱ መናገር ሲገባው) እረስቶት በዚያው ጊዜ ንግግሩን ተናግሯል የሚባለውን (ማለትም እራሱን ተደራሽ አድርጎ) ለወጠው፡፡

አላህ ለመሐመድ ሲናገርልብህየሚለው ቃል ትርጉም ይሰጣል፣ ነገር ግንበላቸውየሚለው ትዕዛዝ ከእርሱ በፊት ሲቀመጥ፣ ቀጥሎ ተናጋሪው የሚሆነው መሐመድ በመሆኑ፣ መናገር የነበረበትልቤነበር እንጂልብህበማለት አልነበረም፡፡ አለበለዚያ ግን መሐመድ የታዘዘው ለአዳማጮቹ እንዲናገር ነበር ማለት ነው፣ እንደዚያ ከሆነ ደግሞ መሆን የነበረበትገብርኤል መገለጡን በልባችሁ ላይ አምጥቶታልማለትም የአዳማጮቹልብእንጂየእሱ ልብአይሆንም ነበር፡፡

በቁርአን ውስጥ ያለው የዚህ ጥቅስ ግዴለሻዊ አቀነባበር፣ የመጽሐፉ ጸሐፊው ሰው እንደሆነ ያጋልጣል፡፡ ሰዎች አንድን ነገር በአንድ መልክ ለማለት ፈልገው በሌላ መልክ መጻፋቸው የተለመደና የታወቀ ነው፣ ውጤቱም በትክክል የሚያሳየው በመጀመሪያ እንዲሆን የታቀደው እና በመጨረሻም እንዲሆን የተፈለገው ነገር ነው፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ጸሐፊው ምን ለማለት እንደፈለገ አሁንም እንረዳዋለን፡፡ ይሁን እንጂ 2.97 ላይ ያለው ዓይነት ድብልቅ አቀነባበር በሰዋሰዋዊም ሆነ በቃላት ትርጉም አቀነባበርና አጠቃቀም መሠረት ትርጉመ ቢስ ነው፡፡

ይህ ጥቅስ 2.97 ትርጉመ ቢስ ሆኖ ለዘላለም እንዳይቀርና ትርጉም እንዲሰጥ ለማዳን ካስፈለገ በዝቅተኛ የሚከተለው ጥረት መደረግ አለበት፣ ይህም በጅማሬው ላይ ያለውበላቸውየሚለውን ቃል ማስወገድ፣ ወይንም ደግሞ ለልብ የተጨመረውን ተውላጠ ስም መለወጥ አለበት ማለት ነው፡፡

ምንም እንኳን በመጨረሻው ላይ እያንዳንዱ ሰው ወደራሱ መደምደሚያ ቢመጣም እኔ ግን እንዲህ ዓይነት የተሳሳተ የዓረፍተ ነገር አቀነባበር ሁሉን አዋቂ፣ ጥበበኛ፣ እና ፍፁም ከሚባለው እግዚአብሔር ከሆነው አምላክ የመጣ ነው የሚለውን ለመቀበል አስቸጋሪ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ እንዲሁም ከአላህ ዘላለማዊ የጽሑፍ ሰሌዳ ላይ ከሰማያዊው ቁርአን ላይ ኮፒ ተደርጎ ለመሐመድ ከመሰጠቱ በፊት በገብርኤል ኮፒ ተደርጎ ነው የሚለውን ለመቀበል ይቸግረኛል፡፡ ነገር ግን ይህ የሰው ስህተት ነው፣ ቁርአንን ባቀናበረው ሰው የተፈጠረ ስህተት ነው፣ ቢባል ግን የበለጠ አሳማኝ ይሆን ነበር፡፡

ይህ ጥቅስ ማለትም 2.97 የቁርአን ጸሐፊ እግዚአብሔር ላለመሆኑ አንድ ተጨማሪ ማስረጃ ነው፡፡ ይህ አቀነባበር የመጣው ለስህተት ክፍት ከሆነው ከሰው አዕምሮ ነው ማለትም ሁሉም ቁርአን ከሰው የፈለቀ ነው ባንልም እንኳን ቢያንስ የተወሰነው የቁርአን ክፍል የመጣው ግን ከሰው አዕምሮ ነው፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡-

ከዚህ በላይ ያየነው ጽሑፍ የተመሠረተው በቁርአን አንድ ጥቅስ 2.97 ላይ ነው፡፡ ጥቅሱን በአንክሮ የሚመከለት እና ጠያቂ አዕምሮ ያለው ሰው እንደሚያስተውለው፣ ጥቅሱ ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከሰው አዕምሮ እንደመነጨ ነው፡፡ ትርጉም አይሰጥም የቋንቋንም ሕግ የጠበቀ አይደለም፡፡ ይህ እውነታ ደግሞ አንድ መሠረታዊ ጥያቄን ማስነሳት ይኖርበታል፡፡ ቁርአን ከእግዚአብሔር የመጣ ካልሆነ፣ እንደዚህ ዓይነት ስህተቶችም የሞሉበት ከሆነ ወደ እግዚአብሔር እንዲመራኝ እንዴት ልታመንበት እችላለሁኝ? የሚለው ነው፡፡

ወደ እግዚአብሔር መቅረብና የእሱ ተከታይ መሆን አስደናቂና ታላቅም ዕድል ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን ቅዱስ ነው፣ ፍፁምም ነው፣ ወደ እርሱ መቅረብም የሚቻለው እራሱ ባዘጋጀው የደኅንነት መንገድ ብቻ ነው፡፡ ይህም የእርሱ የደኅንነት መንገድ በጣም ግልጥ ነው፣ ውስብስብም አይደለም፡፡

ለኃጢአተኞች መዳን የእግዚአብሔር መንገድ የሆነው በመስቀል ላይ የኃጢአትን ቅጣት የወሰደው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ መንገድ እውነትና ሕይወት ነው፣ በእርሱ ብቻ ነው ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የሚቻለው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅንና የዘላለም ሕይወትን በነፃ ለማግኘት እንድትችሉ አሁን ለሚቀርብላችሁ ጥሪ እንቢተኞች አትሁኑ፡፡ በግል ሕይወታችሁ ንስሐ ግቡና በጌታ በኢየሱስ በኩል የኃጢአትን ይቅርታ እንዲሰጣችሁና እንዲቀበላችሁ እግዚአብሔርን ለምኑት፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል በገለጠው ብዙ ምህረቱ አማካኝነት ይምራችኋል፣ ይቀበላችኋልም፣ ጌታ እግዚአብሔር ይርዳችሁ አሜን፡፡

 

የትርጉም ምንጭ: The Stray Say: How the author of the Qur'an messed up, Jochen Katz

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ