አጫጭር ዜናዎች

 

የእስላም አክራሪዎች የንግግርን ነጻነት እያፈኑ ነው!

አንድ ልጅ እስልምንና ተሳድበሃል ተብሎ በግብጽ እስር ተፈረደበት

የአለም አቀፍ የክርስትና ተቆርቋሬ (ICC) ድርጅት እሮብ (April 4, 2012) የግብጽ ፍርድ ቤት እስላምንና ተሳድበሃል ብሎ በአንድ ልጅ ላይ የሶስት አመት የእስራት ፍርድ ማስተላለፉን ለማወቅ ችሏል። ይህ ጉዳይ ባለፉት ቅርብ ወራት በክርስቲያኖችና በለዘብተኛ እስላሞች ላይ የቀረቡትን እስልምናን አዋርዳችኌል የሚሉ ክሶችን ተከትሎ የመጣ ሲሆን፤ የእስልምና አክራሬዎች በአሁኑ ጊዜ ያገኙትን የፖለቲካ ስልጣን በመጠቀም የንግግር ነጻነትን እያፈኑ የመሆኑ አሳሳቢነት አባብሶታል፡፡

የ17 አመት ወጣት የሆነው ጋማል አብዶ ማሱድ በፌስ ቡክ ላይ ያወጣው  የካርቱን ስዕል ሙስሊሞችን የሚያስከፋ ተደርጎ በመወሰዱና በላይኛው ግብጽ ግዛት በአሲዩት ላሉ ለትምህርት ቤት በመበተኑ የግብጽ ፍርድ ቤት በ(April 4, 2012) ቅጣት ወሰኖበታል።  በታህሳስ ወር የወጣው የካርቱን ስዕል ለሁለት ቀናት የቆየ ተቃውሞ ስልፍን በአጎራባች መንደሮች ውስጥ አስነስቶ ነበር፡፡ በብጥብጡም ጊዜ ብዙ የክርስቲያን ቤቶች ሲቃጠሉ ብዙ ክርስቲያኖችም የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ነበር።

በ December 31 የመንደሩ ተደማጭነት ያላቸው አዛዉንቶችና የሳላፌስ(አክራሬ የሳዉዲ ዋሃቢ እስልምናና ትምህርት ተከታይ ቡድን) ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢው ፓሊስ ማሱድን ጠብ አነሳስተሃል በማለት ከሰውት ነበር። የአሲሬያን አለም አቀፍ የዜና ወኪል እንደዘገበው ሁሎም ማሱድን ለማሰርና ቤተሰቡን ከመንደሩ ለማባረር ተማምተው እንደነበር ዘግቧል፡፡ ማሱድም የሦስት ዓመት እስራት ፍርድን ትናንትና ከፍርድቤት ከመቀበሉ በፊት ለሶስ ወራት በእስር ቤት ቆይቶ እንደነበረ ተዘግቧል፡፡

በሬውተር የዜና ወኪል የታየው የፍርድ ቤቱም ውሳኔ እንደሚከተለው፤ «የአሲዩት የህጻናት ፍርድ ቤት ጋማል አብዶ ማሱድ እስልምናን ስለዘለፈ እንዲሁም ነቢዩንና እስልምናን የሚያዋርዱ ምስሎችን አውጥቶ ስአሰራጨ ለሶስት አመት እንዲታሰር ወስኖበታል» ይላል። የሰብአዊ መብት ሕግ አዋቂው ነጋድ አል-ቦራይ እንዳለው ይህ  የእስር ፍርድ በግብጽ ህግ መሰረት እስልምናን ለዘለፈ የሚሰጥ ከፍተኛው  ቅጣት ነው ብሏል።

የማሱድ ጉዳይ ባለፉት ቅርብ ወራት በክርስቲያኖችና በሃይማኖት ገለልተኞች ላይ የቀረቡትን እስልምናን አዋርዳችኌል የሚሉ ተመሳሳይ ክሶችን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ በ January 9, ክርስቲያንና ትልቅ የስልክ ድርጅት ባለንብረት የሆነው ናጊብ ሳዊሪስ ነጻ ግብጻውያን የሚለውን የፖለቲካ ፓርቲ የመሰረተው ሰው፣ ፂማም አይጥና ፌቷን የተሸፈነች ትንሽ አይጥን ካርቱኖችን በትዊትር ላይ  በድጋሚ አውጥተሃል ስለዚህም “እስልምናን ተሳድበሃል አዋርደሃል» ተብሎ ተከሶአል። የግብጽ ፍርድ ቤትም በMarch 3 ሁለተኛውን ክስ ውድቅ ቢያደርገውም አሁንም በሳዊሪስ ላይ የተንጠለጠሉት ክሶች እንዳሉ ናቸው። ሌላው በእንጥልጥል ላይ ካሉ ክሶች አንዱ ደግሞ በታዋቂው የግብጽ የኮሜዲ ተዋናኝ በአዴል ኢማም ላይ የተፈረደውና በይግባኝ ሂደት ላይ የሚገኘው የሶስት ወር እስራት ፍርድ እንደገና በግምገማ ላይ ነው፡፡ ክሱም በ2007 በወጣው የኮሜዲ ፊልም ላይ በነበረው ሚና ላይ «እስልምናን አዋረደኻል» የሚል ነበር፡፡

ብሬ ሩቢን የአለም አቀፍ ጉዳዮች ምርምር ማዕከል (GLORIA) ዳይሬክተር እንዳለው “ጦርነቱ በእርግጥ እየታወጀ ያለው፤ ተቀባይነት ሊኖረው የሚገባው የሃይማኖት አተረጒጎም የእነሱ ብቻ እንዲሆን በሚፈልጉት በእስልምና አክራሪዎች ነው”፤ በመቀጠለም እንዳለው «ያ በሚሆንበት ጊዜ ማንኛውም በጣም ዘመናዊ ወይንም ለዘብተኛ ባህላዊ አመለካከት ሁሉ ህገ ወጥና ቅጣት ማስከተሉን ምዕራባውያን አልተረዱትም። የእስላምና አክራሪዎች ጸረ የመብት አንቀጽ እንደሚያውጀው የአገሪቱ ህዝብ  በነጻ የመሰብሰብ የመጻፍ የመናገር  መብት ወይም የሃይማኖት ነጻነት የለውም»።

«የሚያሳዝነው እስልምናና አዋርደሃል የሚሉ በጋማል አብዱ ማሱድ ላይ እንደቀረቡ አይነት ክሶች በየጊዜው ኢየበዙ እንደሚመጡ ነው። የእስልምና አክራሪዎች በሙስሊም ወንድማማቾች መሪነትና ከፍተኛ የሳላፊ ተከታዮች ድጋፍ በግብጽ ፓርላማ ወስጥ የበላይነትን በማግኘት በአሁኑ ጊዜ የግብጽን ህገ መንግስት በመጻፍ ሂደት ውስጥ ወሳኝ ሆኖአል። ከዚህም በላይ በመጪው ግንቦት የፓርላማ ምርጫ የእስልምና አክራሪዎች የፕሬዘዳንትነትን ምርጫ የማሸነፍ ከፍተኛ እድል አላቸው። የእስላም አክራሪዎች የመንግስት ስልጣን ሲያጠናክሩ የማይቀረው ነገር እስልምና በግብፅ ህግ መሰረታዊዊ ተፅዕኖ መሆኑ ነው።  በአሁኑ ጊዜ የግብጽን ሙሉ በሙሉ ወደ እስላም አገርነት መቀየርን የገታው ብቸኛ ኃይል ምናልባትም የጦር ሃይሉ ይሆናል። ዳሩግን የጦር ሃይሉ በስልጣን እያለ የእስላም አክራሪዎች በንግግር ነጻነት ላይ ጥቃት ካደረሱ ሙሉ ቁጥጥር ሲኖራቸው ጥቃቱ ምን ያህል የከፋ ይሆናል? ከአንድ አመት በፊት ፕሬዘዳንት ሙባሪክን ከስልጣን እንዲገለል የታገሉት ለዘብተኛ የሆኑ የመብት ተሟጋቿች ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍለው የተዋጉለትና የተከላከሉለት ነጻነት በእስልምና አክራሪዎች እየተደመሰሰ መሆኑ በጣም ያሳዝናል» በማለት የመካከለኛው ምስራቅ የአለም አቀፍ ክርስቲያን ተቋርቌሪ ድርጅት የክልሉ ሃላፊ አይዳን ክሌይ ተናግሯል።

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

በግብፅ ውስጥ እየሆኑ ካሉት ነገሮች አንዱና የቅርቡ በ17 ዓመት ልጅ ላይ የተፈረደው የሦስት ዓመት እስራት ነው፡፡ የልጁ ወንጀል በፌስ ቡክ ላይ ያቀረበው ካርቱን እስልምናን ይሰድባል የሚል እንደሆነም ተገልጧል፡፡ እንደሚታወቀው የቅርቡ የግብፅ የሕዝብ እንቅስቃሴ ዋና ዓላማው የሰብዓዊ መብት መከበር፣ ሰላምና ነፃነት መስፈኑ እንደነበረና ግብፃውያን ሁሉ ያለ ምንም የሃይማኖት ልዩነት ተሳትፈውበታል፡፡ አሁን በተግባር የሚታየው ግን ከታሰበው በጣም የራቀ እውነታ ነው፡፡ ይህም ሁላችንም ይህ ለምን ይሆናል የሚል ጥያቄን እንድንጠይቅ ይገፋፋናል፡፡
ሙስሊሞች በተለይም አክራሪዎች በየትኛውም አገር ስልጣንን ቢይዙ ከዚህ የከፋ እንጂ የተለየና የተሻለ ነገር እንደማይመጣም ያሳስበናል፡፡ የዚህ ገፅ አዘጋጆች ፖለቲከኞች ባንሆንም የሰው ልጅ ስቃይና ሰቆቃ ይዘገንነናል አንድ ሃይማኖት ለሰዎች መብት ካልቆመ የፈጣሪ ተከታይነቱም አይታየንም፡፡ ስለዚህ አንባቢዎችን ወደ መጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር እንዲመለሱ ለሰዎችም ሰላምና ደህንነት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ ከእግዚአብሔር ዘንድ እርዳታን እንዲቀበሉ እንጋብዛለን፡፡ እግዚአብሔ ይርዳችሁ!

የትርጉም ምንጭ:  "Egypt sends Christian student to jail for insulting Islam" (ICC) "Egypt sends Christian student to jail for insulting Islam" (Reuters)

 

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ