የቁርአን ውጪያዊና ውስጣዊ ሁኔታ ሲገመገም

በJay Smith

[ክፍል አንድ] [ክፍል ሁለት]

ትርጉምና ቅንብር በAI አማርኛ ቡድን

ቁርአን የተቀበሉት ሕዝቦች፣ ቁርአን ከሰው ልጆች ታሪክ በላይ የሆነ የአላህ ቃል ነውና ከማንኛውም ግድፈት የነጻ “ከኡሙ አልኪታብ” ላይ ከሰማይ በመሐመድ በኩል አላህ ያወረደው/ተንዚል/ ነው ይላሉ፡፡ እነዚህ ሕዝቦች ሙስሊሞች ናቸው፡፡ ይህ የሰማይ ሰሌዳ ‹አልለውህ አል-ማህፉዝ› እንደሚባልም ይናገራሉ፡፡ በምዕራፍ አልቡሩጅ 21-22 እና አልረዕድ 13-39፣ የከበረና የተጠበቀ በሆነ ሰሌዳ ውስጥ ያለ የመጽሐፍ መሠረት እንደሆነ ተገልጧል፡፡

ቁርአንን በእንዲህ መረዳት የተቀበሉት ሙስሊሞች በምንም መንገድ በእሱ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን አይቀበሉም እንዲነሳም አይፈልጉም፡፡ በአንጻሩ ግን መጽሐፍ ቅዱስን ከዚህ መጽሐፍ ጋር በማነፃፀር ይተቻሉ ያብጠለጥላሉ አልፈውም በስህተት የተሞላ ነው ይላሉ::

በዚህና በሌሎች ጉዳዮች እኛም መጽሐፍ ቅዱስን በአግባቡ የተረዳነው፣ ቁርአንን በውጪያዊና በውስጣዊ ሁኔታዉ ምን እንደሚመስል ተመልክተን ጥያቄዎችን ማንሣት አስፈላጊ እንደሆነ በማመን በሚከተለው ሁኔታ አቅርበነዋል፡፡

ቁርአንን አይነኬ ያደረጉት አማኞቹ እንደሆኑ ሲታይ ርዕሰ ጉዳዩ በዚህ ዘመን በጀርመንና በእንግሊዝ ሀገር ማንሳት በመቻሉ አስገራሚና ጠቀሜታውም የላቀ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ይህንን ጥናታዊ ዳሰሣ ለማድረግ የእንግሊዘኛና አረብኛ እንዲሁም የአረብኛ፣ አማርኛ እና የአማርኛ ቅጂዎችን ተጠቅመናል፡፡ ምክንያቱም ሙስሊም ምሁራንና ሌሎችም አረብኛ ቋንቋ ብቻ የቁርአን ቋንቋ ነው፣ ከዚህ ውጪ ያሉት ሌሎች ትርጉሞች ከቁርአን መልዕክት አንፃር ከአረብኛው ያንሳሉ ብለው ስለሚያምኑና ስለማይቀበሉት ነው፡፡

አረብኛውን የቁርአን መጽሐፍ ለማየት እንዲረዳቸውም የአረብኛ ቅጂዎች ያለውን ቁርአን ተጠቅመናል፡፡ ሊቃውንት ወይም አማኞቹ አረብኛው እንዲህ አይልም በማለት የሚነሱ ጥያቄዎችን ላለመቀበል የሚያደርጉትንም ተቃውሞ አስቀድሞ ለማስቀረት ይጠቅማል ብለን እናምናለን፡፡

የቁርአን አደረጃጀትን በተመለከተ፡- ቁርአን ከ610-632 ዓ.ም ለ22 ዓመታት ለኢስላሙ ነቢይ መሐመድ የተገለጠ /የተወረደ/ መጽሐፍ ነው፡፡ ፈጣሪ አላህ በርሱ ዘንድ ካለው “ከኡሙ አልኪታብ” የመሐፍት እናት ያለምንም ልዩነት ጅብሪል በተባለው መልአክ አማካይነት ለነቢዩ መሐመድ በቃል /በድምፅ/ የተደመጠ፣ የተደገመ፣ የተነገረ፣ በኋላም በጽሑፍ የተደራጀ ፍፁም ስህተት አልባ መጽሐፍ ነው ይላሉ፡፡ መጽሐፉ ከ610-622 ነቢዩ መሐመድ በመካ በነበረ ጊዜ እንዲሁም ከ622-632 በመዲና በቆየበት ጊዜ የመጣለት መልዕክት ነውና የመካና የመዲና ምዕራፎች ተብሎ ተከፍሏል፡፡

የምዕራፎቹ አደረጃጀት ከትልቁ ምዕራፍ ወደ ትንሹ ምዕራፍ /ሱራዎች/ ነው፡፡ ትልቁ ሱራ አልበቀራህ 286 አንቀጾች ሲኖረው ትንሹ‡ /አል አስር/ /አልከወሰር/ /አልነስር/ እያንዳንዳቸው ሶስት ሶስት አንቀጾች ብቻ አሉዋቸው፡፡ ሙስሊሞች ቁርአን ከማንኛውም መለኮታዊ መጽሐፍ የበለጠ ታማኝ እንደሆነም እርግጠኞች ነን ይላሉ፡፡

በአጻጻፉ፣ በዓረፍተ ነገር አቀማመጡ፣ በሚጠቀመው የአረበኛ ቃላት ፍፁም ጥራት ያለው ከማለት አልፈው አረብኛ ቋንቋ በአላህ የተመረጠ የአላህ /ቋንቋ/ ነው እስከማለት ይደርሳሉ፡፡

በአማኞቹ እንዲህ የተወሰነው መጽሐፍ ቁርአን ታዲያ እንደተባለለት ነው ወይ? በማለት ከበርካታ ጥያቄዎች መካከል በዚህ ወቅት ጥቂቶችን እናነሳለን፡፡ በምድር ላይ ካሉት ብዙ ሺህ ቋንቋዎች አረብኛን አላህ ከመረጠ፣ ቋንቋውን የሚሰማው እንደሌለ አድርጐ ስለፈጣሪው ለምን ይናገራል? ደግሞስ ቁርአን ለሁሉም የሰው ልጆች የመጣ መልዕክት ከሆነ ሰዎችን ቢያንስ በሚናገሩት ቋንቋ ስለምን ይለያያል? በማለት እንጠይቃለን፡፡

በመጀመሪያ ቁርአን ልዩ ነው ወይ? /ሚሽካት/ የተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 3 ገፅ 664 እንደገለፀው ከአስደናቂዎች አስደናቂ፣ ተወዳዳሪ የሌለው፣ የክርክር ችሎታው፣ አስተሳሰቡ፣ የሰውን ፍጻሜ የመቅረፅ ችሎታው የላቀ ነው እንደሚለው ነው ወይ?

ብዙ ጊዜ ከሙስሊሞች ጋር በሚደረግ ንግግር ይህ ሐሳብ ከቁርአን በአልበቀራህ ምዕራፍ 37-38፣ 23፣ በአልኢስራዕ ም.ቁ 88ን በመጥቀስ የቁርአን ብጤ ተመሳሳይ ሊመጣ እንደማይችል ይናገራሉ፡፡ እንደ ቁርአን ያለ አንድ እንኳን ሌላ አምጡ ይላሉ፡፡

እኛም መጽሐፍ ቅዱስን አንስተን የመዝሙረ ዳዊት 23ኛ ምዕራፍ በማንበብ ለምሳሌም እንደ ሼክ ዑመር በክሪ ለመሳሰሉት በእንግሊዝ አገር ላሉት የሙስሊም ኮሚኒቲ አባልና ለመሰሎቻቸው ጥያቄዎችን አቅርበናል፡፡ ይህንን የመዝሙረ ዳዊት 23ኛ ምዕራፍ የሚመስል አንድ እንኳን እንዲያመጡ ጠይቀናቸዋል፡፡ ማንኛውም ክርስቲያንም ይህንኑ መሰል ጥያቄን ማቅረብ ይችላል፡፡

በመቀጠልም (መዝሙረ ዳዊት 23) ቁጥር 1-5 እግዚአብሔር እረኛዬ ነው እንደሚለን እርሱ ፈጣሪያችን ብቻ ሳይሆን በሕይወት ዘመናችን በምናልፍበት የኑሮ ምዕራፍ ሁሉ ጠባቂያችንም ጭምር እንደሆነ እንነግራቸዋለን፡፡

እናንተስ ጠባቂ አላችሁ ወይ? የእናንተ አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተገለጠው አምላክ ከእናንተ ጋር በቅርበት ይገኛል ወይ? ብለን እንጠይቃቸዋለን፡፡ በተመሳሳይም የቁርአንን ተመሳሳይ ማቅረብ አይቻልም እንደምትሉ የሌሎችን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ለምሣሌም ያህል (ማቲዎስ ወንጌል ምዕራፍ 5፣ የ1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 13) ተመሳሳይ አቅርቡልን እንላለን፡፡

ቁርአን እንደሚልቅ የተናገራችሁን መጽሐፍ ቅዱስ ተበላሽቷል ብላችሁ ብትደመድሙ እኛም መጽሐፍ ቅዱስ በምድር ላይ እስካሁን ካሉት መጽሐፍት እጅግ የላቀ ስልጣን ያለው ውበት ያለው ሕይወትን ለበጎ ነገርና ለዘላለም ሕይወት የሚያበቃ ሙሉ መልዕክት ያለው እንደሆነ እንመሰክራለን፡፡

ለዚህም ነው ቁርአን ለአማኞቹ እውነተኝነቴን ከተጠራጠራችሁ ለማረጋገጥ ወደ ቀደመው መጽሐፍና ወደ ባለቤቶቹ በመሄድ ጠይቁ በማለት የጻፈው፡፡ በተጨማሪም አልማኢዳህ ም.ቁ.44ና 48 መልዕክቶችን መመልከት ይቻላል፡፡       

የቁርአን የስነጽሑፍ ይዘትን በተመለከተ፡- ቁርአን በስነጽሑፍ ይዘቱ የላቀ ነው ወይ? በንፅፅር ለመመልከት ቁርአን አላህ ሁሉን ተቆጣጣሪ እንደሆነ ይናገራል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ከፍጥረት መጀመሪያ ለአዳምና ለሄዋን ምርጫን እንደሰጠ ያስተምራል፡፡ ቁርአን በሁድ ምዕራፍ 1-2 ስለአላህ ጥበበኛነትና ስለመጽሐፉ ጥንካሬ ተናግሯል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 3 ቁ.16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን በመስጠት ዓለምን እንደወደደና ይህም በዓለም ለመፍረድ ሳይሆን ዓለምን በእርሱ ለማዳን መሆኑን ያስረዳል፡፡ በማቴዎስ ወንጌልም የፍቅርንና የመዳንን መንገድ፣ የፅድቅንም መንገድ ያስተምራል፡፡

ቁርአን በአል ካፌሩን ምዕራፍ 109 ላልተከተሉት የምገዛውን አምላክ ተገዢዎች አይደላችሁም ሲል መፅሐፍ ቅዱስ በመዝሙረ ዳዊት 23 ግን እግዚአብሄር ጠባቂያችን መሆኑን ያስተምረናል፡፡

ቁርአን በአልኑር ምዕራፍ 2 ኃጢአተኛ መገረፍ እንደሚገባው ግርፋቱም ምዕመናን በተሰበሰቡበት ያለ ርህራሄ እንዲፈፀም ያስተምራል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 8 ቁጥር 3-12 ግን ጌታ ኢየሱስ አመንዝራይቱን ሴት አልፈረድብሽም ሂጂ ከእንግዲህ ግን ኃጢአትን ደግመሽ አትስሪ በማለት ምህረትን እንደሰጣት ያስተምራል፡፡ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 5.43 ጠላቶቻቹሁን ውደዱ ለሚያሳድዱችሁ ፀልዩ በማለት አስተምሯል:: 

በተለይ ሴቶችን በአልኒሳዕ ምዕራፍ 34 አልበቀራዕህ ምዕራፍ ቁጥር 4 ማመፃቸውን የምትፈሩትን ገስጿቸው፣ በመኝታ ተለዩዋቸው፣ ምቱዋቸው እያለ የድብደባ መምሪያ ሲሰጥ መጽሐፍ ቅዱስ ግን በአዲስ ኪዳን በኤፌሶን ምዕራፍ 5.22-33 ሚስት ለባልዋ ልታደርግ የተገባውን እና ባልም ልክ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እንደወደደ ሚስቱን እንዲወድ ያስተምራል፡፡

ታዲያ ይህንን መሰል መልዕክቶችን የያዘ መጽሐፍ ሆኖ እያለ እንዴት በመልዕክቱ እንከን የሌለው ተብሎ ይነገራል::

በስነጽሑፍ ረገድም ቁርአን ከሞላ ጎደል የተረከው ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ከኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ ሙሉ ታሪኩን ከምናገኘው ዮሴፍ በስተቀር የአንድን ርዕሰ ጉዳይ መነሻና ፍጻሜ የሚያብራራ የአጻጻፍ ስርዓት የለውም፡፡ ከአንድ ጉዳይ ወደ ሌላው፣ ከአንድ ዘመን ወደ ሌላው፣ ከአንዱ ቤተሰብ ወደ ሌላው፣ በማጣቀስ የተደራጀ መጽሐፍ ነው፡፡ ከመጥምቁ ዮሐንሰ ጀምሮ ወደ ሙሴ ይመለሳል፡፡ ስለ አብርሃም ጀምሮ ስለማይታወቅ ጉዳይ ይተርካል፡፡ 

ቁርአን ራሱን እንኳ አያብራራም፡፡ የመልዕክት ቅደም ተከተል የለውም፡፡ ከአንድ ሀሳብ ወደ ሌላው ሲዘልቅ የቋንቋን ስርዓት በጠበቀ መንገድ የማያያዣ ቃላትን (መስተዋድድና መስተፃምር) አይጠቀምም ግስና ስምን እያመሳቀለ ግራ የሚያጋባ ድግግሞሽ የበዛበት ስለሆነ ማንም ሰው በቀላሉ ሊረዳው አይችልም፡፡ የቁርአን ሊቃውንት እንኳን ሃያ ከመቶውን ወይም አንድ አምስተኛውን ያህል አልተረዱትም፡፡ 

በርካታ ሙስሊሞች ቁርአን አይነኬ፣ አይጠየቄ፣ አይደፈሬ፣ ተደርጎ ስለተነገራቸው ብቻ በጭፍን ድንቅነቱን ይናገራሉ እንጂ በአግባቡ ያልተረዱት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ከአረብኛው ቋንቋ ውጪ የተተረጐሙትን ቁርአኖች ሙሉ ተቀባይነት ስለሌላቸው የአረብኛን ቋንቋ በከፍተኛ ዕውቀት ደረጃ ያልተረዱት ተከታዮቹ አያውቁትም፡፡ እናውቀዋለን የሚሉትም ለራሱ ለቁርአን ማብራሪያ የተዘጋጁትን መጽሐፍቶች ከመቀበል ውጪ መተርጎምም መጠየቅም መተቸት አይፈቀድላቸውም፡፡ 

ሊቃውንት ስለሙስሊሞች መጽሐፍ ስለ ቁርአን የሚሉትንም ስንመለከት ለመረዳት አስቸጋሪ መሆኑን እናረጋግጣለን ‹ስልማንራይደል› የተባለው ጀርመናዊ ተመራማሪ የቁርአንን ስነ ጽሑፋዊ ይዘት ስናየው ትኩረትን የማይስብ ድግግሞሽ የበዛበትና ማን? መቼ? እንዴት? የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ለማጥናት አመቺ ያልሆነ፣ የተጠየቅ እጦት የበዛበት፣ ተከታታይነት በሌለው አንቀፆች የታጨቀ የቃላት ውርጅብኝ ነው፡፡ ቁርአን በማንኛውም ገፅ አንባቢውን ግራ የሚያጋባ በመሆኑ ብዙ ሰዎች እሱን አንብበው ለመረዳት ጊዜያቸውን ሲያውሉ ማየት በጣም ይገርማል ብሏል፡፡ ‹ቴዎዶር ኖልዶኬ› የተባሉት ሌላ ተመራማሪም ቁርአን የተሯሯጠና ግራ አጋቢ አንቀፆችን፣ የደረቁ መልዕክቶች ያሉባቸው ጥቅሶችን የያዘ መጽሐፍ ነው ብለዋል፡፡ 
 

እንግዲህ ስለቁርአን የሚያጠኑ ሰዎች ይህንን መሰል ድምዳሜ ላይ እየደረሱ ቁርአን የእነሱ እንደሆነ የተቀበሉ ሰዎች ግን አመለካከታቸው ሲመዘን ልንል የምንችለው ወይ አልተረዱትም ወይም በጭፍን መረዳት ይገዙለታል ብቻ ነው፡፡ በየቋንቋቸው ያልቀረበላቸውን እንዲቀርብም ያልፈቀደላቸውን መጽሐፍ የአረብኛውንም ቅጂ አንብበው መረዳት ሳይችሉ ቁርአን ድንቅ ነው ለምን ይላሉ?

ቁርአን በአረፍተ ነገር አወቃቀሩ ስህተተ አልባ ነው ወይ? ይህንን ጉዳይ ለአረብኛ ቋንቋ ሊቃውንት መተው ተገቢ ይመስለናል፡፡ ቁርአን በርካታ ስህተቶች እንዳሉበት ተረጋግጧል፡፡ ሙስሊሞች የቁርአን አረብኛ ያልተዳቀለ አረብኛ እንደሆነ ያምናሉ፣ ነገር ግን አስራ አምስት ከሚደርሱ ቋንቋዎች እንደተዋሰ የቋንቋ ሊቃውንት ገልጠዋል፡፡ ከግብፃውያን፣ ከዕብራውያን፣ ከሲሪያን ክርስቲያን፣ ከአርማይክ፣ ከሀበሻ /ግዕዝ/ ቋንቋዎች ተውሷል፡፡

 ይህ የሚያሳየው መጽሐፉ ከሌሎች ቋንቋዎችም ተቀነጫጭቦ የተደራጀ እንደሆነ ነው፡፡ የተውሶ ቃላትን እየተጠቀመ ንፁህ ነው፣ በቀጥታ በጅብሪል አማካይነት እየተነበበ ለመሐመድ ተደምጦ፣ እሱ ደግሞ ለተከታዮቹ ተናግሮት በመጽሐፍነት ለመደራጀት ችሏል ብለን ለመድፈር እንችላለን? የሰማይ ቋንቋ አረብኛ ነው ብለን ከወሰንን ማነው ከተጠቀሱት ቋንቋዎች ቃላትን የተዋሰው? ሙስሊሞች ግን ከአላህ እንደሆነ፣ ሌላ ቋንቋ እንደሆነ ይናገራሉ መተርጎሙንም ይከለክላሉ፡፡

የቁርአን አድሏዊነትን በተመለከተ፡- ቁርአን ለመላው የሰው ልጅ ሁሉ ሳያበላልጥ የመጣ ዓለም-አቀፋዊ መልዕክት ነው ወይ? ቁርአን ለሰው ልጆች ሁሉ ባለማበላለጥ የመጣ ዓለም-አቀፋዊ መልዕክት ነው ከተባለ በአልነሳዕ ምዕራፍ ቁጥር 3 እና 34 ስለሴቶች የሰጠው መልዕክት እንዴት ነው ማበላለጥ የለውም የሚያሰኘው? ከሴቶች ሁለት - ሁለት፣ ሶስት - ሶስት፣ አራት - አራት፣ አግቡ ይልና በቁጥር 34 ደግሞ አመፀኞች ከሆኑ ደግሞ ምቱዋቸው በማለት ያክላል፡፡ ለወንድ አራት ሚስት ሲፈቀድላት ሴቶችን /ሚስቶችን/ መደብደብ ፈቅዷል፡፡ ዕውነት ለመናገር ያህል ቁርአን ለወንዶች አዳልቷል፡፡

ውርስንና ምስክርነትን በተመለከተ የሚለውን መለየት እንችላለን አልኒሳዕ ምዕራፍ ቁጥር 11 ወንድ ከሴቶች ይልቅ ሁለት እጥፍ ብልጫ ያለው ድርሻ እንዲወሰድ ተፈቅዶለታል፡፡ በአልበቀረህ ምዕራፍ 282 ደግሞ አንድ ወንድ እና ሁለት ሴቶች እንደ አንድ ተቆጥረው እንዲመሰክሩ ሲናገር ሴቶቹ አንዷ ስትረሳ አንዷ አስታዋሽ በመሆን የአንድ ሴት ምስክርነት ሲደመር የአንድ አስታዋሽ ሴት ምስክርነት እኩል ይሆናል የአንድ ወንድ ምስክርነት ነው ይለናል፡፡ በጣም የሚገርመውና በቃላት ገለፃና በመልዕክት ይዘት አሳዛኝ የሆነው ደግሞ አልበቀራህ ምዕራፍ 223 ሴቶችን እንደ እርሻ በመመሰል በፈለጋችሁት ጊዜ እረሱቸው የሚለው ነው፡፡ የሴቶች ፍላጎት እዚህ ስፍራ የለውም መሬት መቼም ቢሆን በባለይዞታው ፍላጎት በተፈለገ ጊዜ ይታረሳል ግዑዝ ነውና አይናገርም፡፡ ቁርአን ሴቶችን የገለጣቸው እንደዚህ ነው፡፡

አልአዞዛብ ምዕራፍ 5ዐ ደግሞ መለኮታዊ ነው ከተባለው አላህ የተላለፈ ነው ወይ? የሚያሰኝ መልዕክት ይዞ ይገኛል በምርኮ እጅህ ከጨበጣቸው ምርኮኞቹ የአጎትህን ሴቶች ልጆች፣ የአክስቶችህንም ሴቶች ልጆች፣ የአክስቶችህንም ሴቶች ልጆች፣ /የየሹሜዎችህንም/ ሴቶች ልጆች፣ ማግባት ለአንተ ፈቅደንልሃል -- በማለት ለሌሎች ወንዶች ብቻ ሳይሆን ለራሱ ለመሐመድ ሴቶችን በልዩ ልዩ ሁኔታ ሚስት እንዲያደርግ ይፈቅዳል፡፡ ይህንን ሙስሊም ሴቶች የማንረዳው፣ እንዲገባንም የማንሻው መልዕክት ነው ይላሉ፡፡ የዘመናዊው ሙስሊም ዓለም ሴቶች ይህንን ለመቀበል ፈፅሞ አይፈልጉም፡፡ በልዩ ልዩ ሁኔታ በተፈጠረ ጫና ካልሆነ በስተቀር ይህን እንደ ፈጣሪ መልዕክት ተቀብለን ለመኖር ይቸግረናል ይላሉ፡፡ 

እንዲያውም በአቡዘይድ አል ኸድነ/አላህ ይዘንላቸው/ በተላለፈው ሐዲት #መሐመድ ሴቶችን እናንተ ሴቶች ምጽዋት ስጡ ከእሳት ሰዎች አብዛኞቹ እናንተ መሆናችሁን አይቻለሁና $ ሲሏቸው የአላህ መልክተኛ ሆይ ስለምን ይሆን ብለው ጠየቁ #እርግማን ታበዛላችሁ ዝምድናን ትክዳላችሁ የአእምሮና የሃይማኖት ጉድለት ያለባችሁ ሆናችሁ አያለሁ አሏዋቸው ሴቶቹም ጉድለታችን ምኑ ላይ ነው ሲሉ ጠየቁ መሐመድም #ይህ የሃይማኖት ጉድለት ነው አሏቸው$ በማለት ዘግበዋል፡፡ ይህን ዘገባ ፊቅህ ስሱንና በሚባለው መጽሐፍ ላይ በሺክ ሰይድ ሳቢቅ የተዘጋጀው ነው፡፡ በዚህ ክፍለ ዘመን ከተጠናቀሩት አበይት የፊቅህ መድበሎች ዋነኛው ነው እርሱም 18ዐዐ ገጾች ያሉት ሶስት ጥራዝ ነው፡፡ 

አሁን ትኩረታችን የሙስሊም ሴቶች መብት ጉዳይ አይደለም፡፡ ነገር ግን ይህ የማያዳላ የፈጣሪ ቃል የተባለው ቁርአን የያዘው የታወቀ መልዕክት ከሆነ መመለስ ያለበት ጥያቄ ነውና አቅርበነዋል፡፡ የጭፍን ድርቅና መልስ አያዋጣም ቃሉን መለወጥ አይቻልምና፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን መልዕክት ስንመለከት ደግሞ በዘፍጥረት 2ኛ ምዕራፍ ቁጥር 19 አንድ ሚስት ለአንድ ባል መፈቀዱን ለአዳምም የተሰጠችው አንዲት ሴት ሔዋን መሆኗን ነው፡፡ 

ሰው በኃጢአት ከወደቀ በኋላ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ የገዛ ምኞቱንና ፈቃዱን በመከተል ከፈፀመው ድርብርብ ጋብቻ በስተቀር፣ ከአንድ ሚስት በላይ ማግባትን መጽሐፍ ቅዱስ አይፈቅድም፡፡ በምሳሌነትም የአዳምንና የሄዋንን ሁኔታ እናስታውሳለን፡፡ በኑሮ ረገድም ሚስቶች ከባሎች ጋር በፍቅርና በምክር እንዲኖሩ መጽሐፍ ቅዱስ አጥብቆ ያስተምራል 1ኛ ጴጥሮስ 3.1-7፡፡

የሴቶች ምስክርንትንም ብንመለከት፣ ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ ምስክር ከሆኑት መላእክት ቀጥሎ ሴቶችን ነው መጽሐፍ ቅዱስ በአስደናቂ ሁኔታ የሚያቀርበው፣ በመሆኑም ስለ ማርያምና ስለ መቅደላዊት ማርያም ማቴዎስ 28.2-1ዐ ላይ እናነባለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በሴቶችና በወንዶች መካከል አድልዎ የሌለበትን መልካምነት ያለበትን መልእክትና ትምህርትን በዕብራውያን 4.1፣ 1ኛ ጴጥሮስ 3፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 7 እንዲሁም ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው ኤፌሶን ምዕራፍ 5 ላይ ያቀርባል፡፡ ቁርአን በሴቶችና በወንዶች መካከል አዳልቷል ወይስ አላዳላም? ሁለት ሴቶች እንደ አንድ ወንድ ምስክርነት ወይስ አንዲት ሴት እንደ አንድ ወንድ ምስክርነት ነው ቁርአን ያቀረበው? ሚስትን መደብደብ ወይስ ማፍቀር? ሴቶች የገሃነም እሳት ማቀጣጠያ ወይስ የትንሣኤ ምስክር?

ቁርአን ከመጽሐፍ ቅዱስ 6ዐዐ ዓመታት በኋላ እንደጻፈ ታሪካዊ እውነታ ነው፡፡ ምንም እንኳን “ከኡሙ አልኪታብ” ላይ የተወሰደ ትክክለኛ ቅጂ ነው ቢሉትም በመልዕክቱ ይዘት እንደ መጽሐፍ ቅዱስ እኩል ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም፡፡ ከ4ዐ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከእግዚአብሔር የሰሙትን መልዕክት በ15ዐዐ ዓመታት ጊዜ ውስጥ ቢጽፉትም፣ መጽሐፍ ቅዱስ በመልዕክቱ፣ በአጻጻፉ፣ በጽሑፍ አደረጃጀቱ፣ ዕርስ በርስ ባለው ተያያዥነትና የትኩረት ነጥብ እንዲሁም (ወጥ  የሆነ መልእክት) እውነት እንናገር ከተባለ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚወዳደር መጽሐፍ በጭራሽ የለም፡፡

ኧረ ለመሆኑ የቁርአኑ ገነት በአል ፋጢር ምዕራፍ 33 መሰረት ምን አዘጋጅቷል? የወርቅ አምባሮች ሉልንም የሐር አልባሳት የሚለው ገነት ስጋዊ ወይስ መንፈሳዊ ነው፣ አድራሻውስ የት ነው? በአልርአማን ምዕራፍ 7ዐ-76 በገነት ለወንዶች የተዘጋጁትን ሴቶች ሁኔታ ይናገራል፡፡ ቁጥር 7ዐ በውስጣቸው ጠባየ መልካሞች መልከ ውቦች /ሴቶች/ አልሉ፡፡ ቁጥር 72 በድንኳኖች የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የሆነ ናቸው፡፡ ቁጥር 74 ከእነሱ በፊትም ሰውም ጅኒም አልገሰሳቸውም በማለት ጽፏል፡፡ ቁርአን የገነት ስጦታ የሆኑት ሴቶች እንደሆኑ ያውም ልዩ አይነት ሴቶች እንደሆኑ ይገልፃል፡፡ ለሴቶች የተዘጋጀን ሽልማት ግን አልነገረንም፡፡ ደግሞስ ጂኒ የተባለው ፍጡር በገነት ይገኛል እንዴ፣ ጅኒ አልገሰሳቸውም ማለትስ ምንድነው?

ይህንን ርዕስ ጉዳይ ከመዝጋታችን በፊት በአልአህዛብ ምዕራፍ 33 ሴቶች ከቤት ውጪ መውጣታቸውን ይከለክላል፡፡ በአለባበስ መሸፋፈን እንዳለባቸው አልኑር ምዕራፍ 31 ሴቶችን መፍታት እንደሚችሉ አልጦለቅ ምዕራፍ 1-2 ባልዋን ፈትታ ድጋሚ መታረቅ ከፈለገች ሌላ አግብታ መፍታት እንደሚኖርባት አልበቀራህ ምዕራፍ 229-232 የሚሉትን ስንመለከት፣ በእርግጥ ቁርአን ለሰው ልጆች እኩል /ተቀባይነት/ ያለው መልእክት ነውን? ብለን መጠየቃችንን ግዴታ ያደርገዋል፡፡ 

የዓመፅ አሠራርን በተመለከተ፡- ሙስሊሞች እንዳይነሣ ከሚሹት ጉዳይ የዓመፅ የሽብር አሠራርን ቁርአን ያበረታታል መባሉን ነው፡፡ ቁርአን መነገር በጀመረባቸው የመጀመሪያዎቹ 1ዐ ዓመታት ውስጥ መሐመድ ከመሰደዱ በፊት፣ ማለትም (የመካ) ሱራዎች በሚባሉት ውስጥ ከሞላ ጎደል ሰላማዊ መልዕክቶችን ቢዘገብም በሁለተኛው ክፍል (የመዲና) ሱራዎች በሚባሉት ከመሐመድ ስደት በኋላ ግን የተጋድሎና በጦርነት የማስገደድ መልዕክቶች ሞልተውበታል፡፡

ኢስላም ሠላም ነው የሚሉን የቁርአን ሊቃውንት ሁለተኛውን የቁርአን ክፍል (የመዲና) ሱራዎች እንዴት እየተረጉመ ይሆን? ለምሳሌ በመዲናው ምዕራፍ አልበቀራህ 256 በሃይማኖት ማስገደድ የለም እንዳላለ ሁሉ በአልበቀራህ ምዕራፍ 4 1ዐ6፣ አልነህል ምዕራፍ 1ሀ1 አንቀፆችን ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከርሷ የሚበልጥ ወይም ከብጤዋን እናመጣል የሚል ድንጋጌ በማስቀመጡ የመካውን መልዕክት በመዲናው መልዕክት ለመለወጥ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡ 

ታሪኩ ሲጠና መሐመድ በመካ በነበረበት ወቅት ጦርነት ማድረግ ስላላስፈለገውና በኋለኛው ዘመን ግን በተጋድሉ ጭምር ሃይማኖቱን ለማስፋፋት የተገደደበት ሁኔታ እንዳለ ታውቋል፡፡ ይህ ወቅት በአረቢያ ምድር ከነበሩት አይሁድ ሕዝቦች ጋር ጭምር ሠላም የሰፈነበት ጊዜ ነበር፡፡ የመዲናውን ምዕራፍ አልሣኢዳህ 51 ተመልከቱ #እናንት ያመናችሁ ሆይ ይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ….. ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከእነርሱ ነው አላህ አመጠኞችን ሕዝቦች አያቀናም$ ይላል፡፡

የሠላም ወቅት አንቀፆች በጦርነት ወቅት አንቀፆች ተለወጡ ተባለ፡፡ እንግዲህ የመካ አንቀፆች በ23 ዓመታት ውስጥ መሐመድ በሕይወት እያለ ከተሻሩ ዛሬ ላለው ሁኔታ የሠላም አቀፆች የተባሉት እንዴት ስልጣን ይኖራቸዋል? እውነቱ የመካ ሡራዎች በ1ዐ1 በጦርነትና በተጋድሎ የመዲና ሱራዎች መልዕክት ተሽረዋል የፊተኞቹ ደካማ ምዕራፎች በኋለኞቹ ጠንካራ ምዕራፎች ተተክተዋል፡፡ ይህን የአንቀፆች የሽረት ሽረት ሕግ እንበለው ይሆን? 

ለምሳሌ በአልበቀራህ ምዕራፍ 19ዐ-193 ላይ ያለውን እንመልከት፡፡ ሊጋደሉዋችሁ ሲመጡ ተጋደሉዋቸው ወሰንንም አትለፉ የሚል መልዕክት ይሰጥና ቀጥሎ ደግሞ ባገኛችኋቸው ቦታ ሁሉ ግደሏቸው አውጧቸው የሚል ተቃራኒ መልዕክት ያስከትላል፡፡ እንግዲህ በአንቀፆች የሽረት ሕግ በ/ናሲክና መንሱክ/ የቁርአን ስነ አተረጓጎም መሠረት የቀደመው ክፍል ተሽሮ የግድያው ትዕዛዝ ይፀድቃል ይተገበራል ማለት ነው፡፡ 

የቁርአን አስቸጋሪነት ይህ ነው፣ ይህም አንድ አንቀፅ በመያዝ እንኳን መልዕክቱ ይህ ነው ለማለት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም በሰላም ጀምሮ በግድያ ይደመደማልና፡፡ 

በተጨማሪም አልማኢዳህ ምዕራፍ 32ትን እንመልከት በእስራኤል ልጆች መካከል ጥፋተኛ ያልሆነን ነፍስ የገደለ የሰውን ዘር ሁሉ እንዳጠፋ ይቆጠራል፡፡ አንዲትን ነፍስ ሕያው ያደረገ (ያዳነ) ደግሞ የሰው ልጆችን ሕያው እንዳደረገ ይቆጠራል ይልና ከዚያ በመቀጠል ደግሞ ብዙዎች በምድር ላይ ወሰን አላፊዎች ሆነዋል በማለት በ33ኛው አንቀፅ ቅጣታቸው መገደል ወይም መሰቀል ወይም እጆቻቸውንና እግርሮቻቸውን በማፈራረቅ መቁረጥ ወይም ከሀገር ማባረር ነው፣ ይህ ለእነሱ በዚህች ዓለም ውርደት ሲሆን በመጪው ዓለምም ታላቅ ቅጣት አለባቸው ይለናል፡፡ 

ይህ አንቀፅ ስለምንድነው የሚያወራው? ተብለው ሲጠየቁ አላህንና መልዕክተኛውን የሚዋጉትን በማንኛውም አገርና ሁኔታ መዋጋት እንደሚገባ ያስተምራል ይላሉ፡፡ ነገር ግን በተለይ እስራኤልን (አይሁድን) ለመግደል ለማሰቃየት የተደነገገ እንጂ ሌላ እንዳይደለ ግልፅ ነው፡፡ 

አትተወባህ ምዕራፍ 5 ላይ ደግሞ አጋሪዎችን ባገኛችኋቸው ቦታ ሁሉ ግደሏቸው ክበቧቸውም (በሚያልፉበት) ጎዳናዎች ሁሉም በንቃት ጠብቋቸው ሲል በቁጥር 14 ደግሞ ተጋደሏቸው አላህ በእጆቻችሁ ይቀጣቸዋል ያዋርዳቸዋል እናንተንም በነርሱ ላይ ድልን ትቀዳጅ ዘንድ ይረዳችኋል የአማኞችን ሕዝቦች ልባቸውንም ያፀናል፡፡ በማለት የሰጠው ትምህርት በርግጥ የሰላም መልዕክት ነውን? ብለን እንጠይቃለን፡፡ በአልአንፋል ምዕራፍ 39 ሁከት ሙሉ በሙሉ እስኪጠፋና ሥርዓት ሁሉ የአላህ እስኪሆን ድረስ ተጋደሏቸው የሚለውስ በርግጥ የሰላም መልዕክት ነውን? 

የጦርነትና የግድያ ትዕዛዛትን በመሐመድ ምዕራፍ 4 የውጊያ አፈፃፀም መመሪያ ይሰጣል፡፡ እነዚያን የካዱ ሰዎችን (ውጊያ ላይ) በምታገኗቸው ጊዜ አንገቶቻቸውን ምቷቸው ባደከማችኋቸውም ጊዜ ማሰሪያዎችን አጥብቁ፣ ማርኳቸው በማለት የጦርነትን ስልት ያስተምራል ይህ በእርግጥ የሰላም መልዕክት ከሆነ የሰላም ደግሞም የሰላማዊነትስ ትርጉም እንግዲህ ምንድነው? ብለን እንጠይቃለን፡፡ ደግሞስ የአላህ ቃል ልዋጭ አለው ወይስ የለውም? ብለን እንጠይቃለን፡፡ ዮንስ ምዕራፍ 6፣ አልአላኢዎ ምዕራፍ 34 

በኢየሱስ ክርስቶስም ሆነ በሐዋርያት የተነገረው የወንጌል መልእክት አንድም ጊዜ ሰዎችን በማስገደድ እንቢ ቢል በመግደል የእግዚአብሔርን እውነት ለማስረፅ የሚሰጠው ቃል የለም፡፡ እንዲያውም ጌታ ኢየሱስ ሰይፍን የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ በማለት ጴጥሮስን ገስፆት ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ ካለ በኋላ ጴጥሮስ በሰይፉ የቆረጠውን ጆሮ መልሶ እንደፈወሰ በወንጌል ተጽፎ ይገኛል፡፡ እንግዲህ ቁርአን እምነቱን በሌሎች ላይ ለመጫን ተጋድሎን፣ ሰይፍን ማሰቃየትን ተጠቅሟል አሁንም እየተጠቀመ መሆኑንም እያየን ነው፡፡ 

በዘመናችንም ብዙዎቹ አጥፍቶ ጠፊዎች የሚጠቅሱት ክፍሎች የአልኒሳ ምዕራፍ 74 እና የመሐመድ ምዕራፍ 25-26 ነው፡፡ ይህ አያስደንቅም በቁርአን የመጨረሻውና ከፍተኛው አስተምህሮት የመዳን መንገድ ማለትም ከዘላለም ቅጣት የመትረፊያ መንገድ ጅሃድ ብቻ ነውና፡፡ 

በእስልምና ጀሃድ መግደል ወይም ገድሎ እስከ መገደል ያለው መንገድ የጀነት መግቢያ ተደርጎ ስለሚማር አንድ የሃይማኖቱ ሰው በዚህ ማለፉ አያስደንቅም፡፡ እንዲያውም ለተማረው ትምህርት ራሱን እስከ ሞት ሰጥቶ ላላየውና ለማያውቀው ነገር መስዋዕት አድርጎ መስጠቱ የአስተምህሮቱን ጥልቅ መንገድ ለማየት ያስችላል፡፡ 

ሙስሊሞች ከዚህ መምሪያ ውጪ ሊሆኑ እንዲሁም አንስማማም ሊሉ አይችሉም፡፡ የቁርአንን መልዕክት እንዳለ መተግበር የእያንዳንዱ ሙስሊም ሰው ግዴታ ነውና፡፡ በአጠቃላይ ከመዲና ሱራዎች አብዛኞቹ ስለ መግደል መጋደል ስለ ሰይፍ የሚናገሩ ናቸው፡፡

ወደ ክፍል ሁለት ይቀጥሉ።

 

Critique of the Qur'an: internal and External critiques, Jay Smith

 ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ