ክርስትያኖች በቁርዓን

M. J. Fisher, M.Div.

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

ቁርአን ክርስትያኖችን በተመለከተ አጅግ ብዙ የሚላቸው ነገሮች አሉት፡፡ እነዚህም እዚህ በተሰበሰቡት በሠላሳ ሦስት ጥቅሶች ውስጥ ሊብራሩ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች መሐመድ ከክርስቶስ እርገት ስድስት መቶ ዓመታት በኋላ ስብከቱን በመጀመሩ ይደነቃሉ፡፡ መሐመድ ወጣት እያለ  የሚያምነውን ነገር ያፈላልግ በነበረበት ጊዜ እምነታቸውን የሚለማመዱ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱሳቸውን በሚገባ ያጠኑ የነበሩ ክርስትያኖች በአካባቢው ነበሩ፡፡ እንዲሁም እጅግ ብዙ የሆኑ አይሁዶችም ነበሩ፡፡

መሐመድ እነዚህን በአንድ አምላክ የሚያምኑ ሁለት ሃይማኖቶችን በትክክል ያውቅ ነበር፡፡ ነገር ግን የካአባን ሃላፊነት የወሰደው ደግሞ የእሱ ጎሳ ነበረ፡፡ ካአባ በጣም ትልቅ ግንብ ሲሆን በውስጡም በመካ በሚገኙ ጣዖታት ሁሉ የተሞላ ነበረ፡፡ የእሱም ጎሳ እንደሚያምነው የእነዚህ ጣዖታት ሁሉ አለቃ የነበረው ጣዖት ‹አላህ› የሚባለው ነበረ፡፡ መሐመድ አላህ ብቻ ነው ብቸኛ የዓለም ፈጣሪ በማለት ባወጀበት ጊዜ አይሁዶችም ክርስትያኖችም ከእነ አብርሃም ዳዊትና ኢየሱስ ጋር እኩል የሆነ ነቢይ መጣ በማለት ይቀበሉኛል የሚል ግምት ነበረው፡፡

ይህንንም እውነታ የሚያሳየው የእሱ የመጀመሪያ ጥቅስ ነው፡፡ በመጀመሪያው አካባቢ ክርስትያኖችና አይሁዶች ‹የመጽሐፉ ሕዝቦች› ተብለው ክብርን ተሰጥቷቸዋል፡፡ መሐመድ የተናገራቸው ጥቅሶች ተቀባይነትን ያገኙት መሰረታቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስላደረጉ ነው፡፡ የሁለቱም እምነት ተከታዮች ማለትም ክርስትያኖችም አይሁዶችም መሐመድን እና ጥቅሶቹን ባልተቀበሉ ጊዜ ቁርአን ተቀልበሶ እነሱንና እምነታቸውን ማጥቃት ጀመረ፡፡ ክርስትያኖችን በተመለከተ በቁርአን ውስጥ ያለው ግጭትም ምክንያት መነሻው ይህ ነው፡፡ ይህንንም በተመለከተ በመጀመሪያ የተነገረውንና መስተመጨረሻም የተነገረውን ወስዶ ፈጣን ንፅፅር ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡ በ2.62 ቁርዓን የሚናገረው ክርስትያኖችና አይሁዶች በፍርድ ቀን ሽልማት እንደሚጠብቃቸው ነው፡፡ በ98.6 ላይ ደግሞ በምድር ላይ ያሉ እጅግ በጣም ክፉ ፍጡራን ተብለው ተጠርተዋል፡፡

ስለዚህም ስለ ክርስትያኖች ቁርአን የሚከተሉትን ይናገራል፡-

ለክርስትያኖችና ለአይሁዶች ሽልማት ይጠብቃቸዋል፡- ሙስሊሞች የሆኑት እነዚያ አይሁዶች ክርስትያኖችም እና ሳባውያን የሆኑት በአላህ ስላመኑ በመጨረሻው ቀን ሽልማት ይጠብቃቸዋል ስለዚህም መፍራትም ሆነ ማዘን የለባቸውም ስለዚህም መልካምን ይስሩ 2.62፡፡

ቀጥተኛ ደቀ መዛምርት፡- አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ቅዱሳት መጽሐፍትን ያስታውሳሉ ይህም በማታና በጠዋት ሲሆን ለአምልኮም ይሰግዳሉ፡፡ እነሱም በአላህና በመጨረሻው ቀን አምነዋል ስለዚህም ፃድቃን ናቸው፡፡ እነሱም ይሸለማሉ፡፡ 3.113-115፡፡

እግዚአብሔርን በግል ስለማወቅ፡- አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው ያለው፡፡ ክርስትያኖችና አይሁዶች ልጆቻቸውን እንደሚያውቁት ያህል ያውቁታል፡፡ ነገር ግን ሌሎች በጣዖት አምልኮ አማካኝነት ነፍሶቻቸውን ስላጡ ስለ አላህም ሐሰትን ስለፈጠሩ በኃጢአት ባህርይ ስለሚኖሩና መገለጥንም ስለሚክዱ ነው 6.20-22፡፡

ተጠራጣሪዎች ወደ አይሁዶችና ወደ ክርስትያኖች ተመርተዋል፡-አንተ መሐመድ የቁርአንን እውነተኝነት የምትጠራጠር ከሆነ እነዚያን መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነቡትን መጠየቅ አለብህ ይህም ከአንተ በፊት የተገለጠውን ነው› 10.94፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ በክርስትያኖችና በአይሁዶች ይጠና ነበር፡- ቅዱስ መጽሐፍን የወረሱት እነዚያ አጥንተዋቸዋል በሚገባም ያውቋቸዋል ስለዚህም ስለ አላህ ትክክል ያልሆነን ምንም ነገርን አያደርጉም 7.169፡፡ ክርስትያኖችና አይሁዶች አንድ አይነትን መጽሐፍ ቅዱስን ስለማጥናታቸው ግን አይስማሙም 2.113፡፡

የኢየሱስ ተከታዮች ታዝኖላቸዋል፡- ኢየሱስ የማርያም ልጅ በሐዋርያትና በነቢያት ረጅም መስመር ተከትሏል፡፡ እሱም ወንጌል ተሰጥቶት ነበር አላህም በእሱ ተከታዮች ልብ ላይ ርህራሄንና ምህረትን አደረገ 57.27፡፡

አንድ አምላክ፡- ለመጽሐፉ ሰዎች ንገራቸው እናንተ ሙስሊሞች ለእነሱ በተሰጠው ቅዱስ መጽሐፍና ለእናነተ በተሰጠው በቁርአን እንደምታምኑ ንገራቸው፡፡ እንዲሁም የእነሱ እግዚአብሔርና የእናንተ አላህ አንድ አምላክ እንደሆነ ንገራቸው እንዲሁም እናንተ ለእሱ እራሳችሁን እንዳስገዛችሁ ንገራቸው 29.46፡፡

ለክርስትያኖችና ለአይሁዶች ስላለው ተስፋ፡- የመጽሐፉ ሰዎች የሚያምኑና ከክፉ የሚጠበቁ ከሆነ ይቅር ይባላሉ፡፡ በቶራና በወንጌልም ውስጥ ያሉትን የሚጠብቁ ከሆነ ይሸለማሉ 5.65፣66፡፡ በቶራና በወንጌል ውስጥ ያለውን ትምህርት ካልተከተሉ ግን ምሪትን ሊቀበሉ አይችሉም 5.68፡፡

አይሁዶች ጠላቶች ናቸው - ክርስትያኖች ግን ትሁታን ናቸው፡- እስልምናን እጅግ በጣም በጥብቅ የተቃወሙት አይሁዶችና ፓጋኖች ነበሩ ነገር ግን እራሳቸውን ክርስትያኖች በማለት ይጠሩ የነበሩት በጣም ተወዳጆች ነበሩ፡፡ እነሱም ቄሶችና መነኮሳት አሏቸው እንዲሁም ትዕቢታንም አይደሉም፡፡ እነሱም ቁርአን ሲነበብ በሚሰሙበት ጊዜ እንባ ከዓይናቸው ይመጣ ነበር ምክንያቱም እውነት እንደሆነ አውቀው ነበርና፡፡ ነገር ግን እነዚያ የማያምኑትና የአላህን መገለጥ የሚክዱት ግን ወደ ሲዖል እሳት ይሄዳሉ 5.82-86፡፡

የተለያዩ ክፍሎች፡- በክርስትያኖችና ወይም በአይሁዶች መካከል ምንም ዓይነት የተለያየ ክፍፍል አልነበረም ይህም ቀላል ትምህርትን የሚያስታውሰው የመሐመድ ትምህርት እስከመጣ ድረስ አላህን ማመን እና እሱን ብቻ መታዘዝ ሁልጊዜ መፀለይ እንዲሁም እውነተኛ ሃይማኖት ለሆነው ታክስን መክፈል የሚለው እስከመጣ ድረስ 98.4-5፡፡ የእስራኤል ልጆች በእስራኤል ምድር እንደደረሱ እና እውቀት በተሰጣቸው ጊዜ ወዲያውኑ መከፋፈል ጀመሩ 10.93፡፡

አላህ ምንም ወንድ ልጅ የለውም፡- አላህ ወንድ ልጅ አለው በማለት የሚያምኑት እነሱ ሊገሰፁ ይገባቸዋል፡፡ ምክንያቱም ይህ እጅግ በጣም አስከፊ የሆነ ስድበ-መለኮት ነውና 18.4-6፡፡ አላህ ምንም ወንደ ልጅ የለውም ከእሱ ሸሪክ የሆነ ምንም አምላክ ከጎኑ የለም 23.91፡፡ አይሁዶች የሚሉት ዕዝራ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብለው ሲሆን ክርስትያኖች ደግሞ መሲሁ የአላህ ወንድ ልጅ ነው በማለት ነው፡፡ አላህ ያጥፋቸው እነሱ ሁለቱም የተጣመሙ ናቸው፡፡ እነሱም መምህራንን መነኩሴዎችን እና መሲሁን የማርያምን ልጅ እንደ ጌታ ከአላህ እኩል ያምናሉ ይህም ደግሞ በአንድ አምላክ እንዲያምኑ ከተሰጣቸው ትዕዛዝ በተቃረነ መልኩ ነው 9.30፣31፡፡

መነኩሴዎች፡- የምንኩስና ተቋማት መኖር ከአላህ አልነበረም ነገር ግን አላህን ለማስደሰት ሰው የሰራው ነገር ነው፡፡ መነኩሴዎች በጥረታቸው የተሳካላቸው አልነበሩም ነገር ግን አንዳንዶቹ ለዚህ እምነታቸው ሽልማትን ተቀብለዋል፡፡ ብዙዎቹም አመፀኞችና ክፉ አድራጊዎች ነበሩ 57.27፡፡

ክርስትያኖችን መዋጋት፡- ሙስሊሞች እስልምናን የሚቃወም ማንንም መዋጋት አለባቸው ይህም አይሁዶችንና ክርስትያኖችንም ጨምሮ ነው ይህም ተከታታይ የገንዘብ ግብር በመስጠት እና ለመታዘዛቸው ፈቃደኛ እስከ ሆኑ ድረስ እና እራሳቸውን ለእስልምና ተዋጊዎች እስካስገዙ ድረስ ነው 9.29፡፡

የገነት (የመንግስተ ሰማይ) ጥያቄ፡- አይሁዶችና ክርስትያኖች የሚሉት እነሱ ብቻ መንግስተ ሰማይ እንደሚገቡ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የምኞት አስተሳሰብ ነው 2.111፡፡

ሦስት ናቸው ማለትን አቁሙ፡- የመጽሐፉ ሰዎች ማጋነን የለባቸውም፡፡ መሲሁ ኢየሱስ የማርያም ልጅ የአላሀ መልክተኛ ብቻ ነው፣ የእሱ ቃል ነው፡፡ በማርያም ውስጥ ከእሱ በሆነ መንፈስ የነፋባት ነው፡፡ ስለዚህም በአላህ እና በመልክተኛው እመኑ እና ሦስት ማለትን አቁሙ፡፡ አላህ አንድ ብቻ ነው፡፡ እሱ እጅግ በጣም ልዩ እና ክቡር ነው ልጅ ሊኖረው አይችልም፡፡ መሲሁም የአላህ ባሪያ ለመሆን በምንም አላፈረም 4.171፣172፣ 5.72፣73፡፡

እንደማያምኑ ተቆጥረዋል፡- የማያምኑቱ እነዚያ አላህ መሲሁ ነው የማርያም ልጅ ነው የሚሉት ናቸው 5.17፡፡

ከክርስትያኖችና ከአይሁዶች ጋር ጓደኝነትን መመስረት አቁሙ፡- ክርስትያኖችን ወይንም አይሁዶችን ጓደኛ የሚያደርግ ሙስሊም ከእነሱ እንደ አንዱ ነው 5.51፡፡

አይሁዶችም ክርስትያኖችም እጅግ በጣም ክፉ ፍጥረታት ናቸው፡- ክርስትያኖች፣ አይሁዶች እና ጣዖት አምላኪዎች በመሐመድና በቁርአን የማያምኑቱ በሲዖል ውስጥ ለዘላለም ይቃጠላሉ እነሱም በምድር ላይ ካሉት ፍጥረታት ይልቅ እጅግ በጣም አስከፊዎቹ ናቸው 98.6፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡-

ከላይ እንዳየነው ቁርአን ክርስትያኖችን በመጀመሪያ ሲደግፍና እንደሚሸለሙ ሲናገር ቆይቶ በኋላ ላይ ማለትም በስተመጨረሻው ደግሞ የተለየ ነገርን ሲያሳይ እንመለከታለን፡፡ ይህንን ጽሑፍ የምታነቡ ሙስሊሞች ሁሉ ቆም ብላችሁ ይሄ ለምን ሆነ ልትሉ ይገባችኋል፡፡ ቁርአን እንዲህ ዓይነትን እጅግ በጣም ፈጣን ለውጥ ለምን አደረገ? ይህንን ዓይነት ትልቅ የአመለካከት ለውጥ የእግዚአብሔር ቃል ሊያሳይ ይችላልን?

እውነተኛውን አምላክ ማወቅና መከተል እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ይህም ሊገኝ የሚችለው ምንም እንከን ከሌለበት ከእግዚአብሔር ቃላ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም ለሕይወታችሁ ዘለቄታዊ ዋስትና ያለውን የምህረትና የዘላለም ሕይወትን ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስን አንብቡ መልክቱንም ተረዱ ጌታ እግዚአብሔርም በቃሉ መሰረት እውነትን ይግለጥላቸሁ፡፡

 

የትርጉም ምንጭ: Christians, Chapter 20 of "A Topical Study of the Qur'an From a Christian Perspective" by M.J Fisher, M.Div

ሙሉ መጽሐፉ በአማርኛ: ርእሳዊ የቁርአን ጥናት በክርስትና አይን ሲመረመር

 

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ